በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጉቴሬሽ ለአፍሪካ ድጋፍ እየለመኑ ነው


የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶንዮ ጉቴሬሽ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶንዮ ጉቴሬሽ

ዓለም “ስለአፍሪካ የሚያደርገውን ንግግር ቃና መለወጥ አለበት” ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አሳሰቡ።

ዓለም “ስለአፍሪካ የሚያደርገውን ንግግር ቃና መለወጥ አለበት” ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አሳሰቡ።

የአፍሪካን እጅግ የገዘፉ ዕምቅ አቅሞች ለመገንዘብ፣ ግጭቶቿን ለመከላከልና በአግባቡ ለመያዝ ሃገሮች ከአህጉሪቱ ጋር ይበልጥ መተባበር እንዳለባቸው ዋና ፀሐፊው መክረዋል።

ግጭቶች እንዳይነሱ በመከላከልና ከተጫሩም የሚያዙበትን ሁኔታ በሚመለከት የአፍሪካ ኅብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተመሣሣይ አቋም እንዳላቸው ጉቴሬሽ ለፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤቱ ዛሬ ሲናገሩ።

“የአፍሪካን አቅም ማጠናከር ለዓለም አቀፍ የሰላምና የደኅንነት ፈተናዎቻችን ለምንሰጠው ምላሽም ሆነ ለአፍሪካ እራሷን የመቻል ጉዳይ እጅግ አስፈላጊ ነው” ብለዋል ጉቴሬሽ።

ሶማሊያ ውስጥ የሸመቀውን አል-ሻባብን ጨምሮ በሽብር ፈጠራና በፅንፈኛ ቡድኖች አፍሪካ ላይ የተደቀነውን አደጋም ጉቴሬሽ አንስተዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ጉቴሬሽ ለአፍሪካ ድጋፍ እየለመኑ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:15 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG