በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመን የምግብ ቀውሱ እንደበረታ ነው


የመን ውስጥ ለዓመታት በዘለቀው ጦርነት በየመን አማፂያኖች የተጎዱ ሕንፃዎች፤ ታኢዝ ከተማ እአአ ሰኔ 9/2022
የመን ውስጥ ለዓመታት በዘለቀው ጦርነት በየመን አማፂያኖች የተጎዱ ሕንፃዎች፤ ታኢዝ ከተማ እአአ ሰኔ 9/2022

እአአ ከሚያዝያ 2 ጀምሮ በመላዋ የመን ሥራ ላይ የዋለው ጊዜያዊ የተኩስ አቁም የተወሰነውን ችግር ረገብ የቀነሰ ቢሆንም የምግብ ቀውሱ እንዳለ ነው አስራ ዘጠኝ ሚሊዮን ሰዎች ለረሃብ ተጋልጠዋል ሲሉ የተመድ ባለሥልጣናት ተናገሩ።

የተመድ የሰብዓዊ ረድዔት አስተባባሪ ቢሮ የኦፐሬሽን ቅስቀሳ ኃላፊ ጋዳ ኤልታሂር ሙዳዊ ሲናገሩ በዩክሬኑ ጦርነት ምክንያት በዓለም ዙሪያ በተፈጠረው የዋጋ መናር በተለይ የየመን ህዝብ ምግብ በጠቅላላ የሚገባው ከውጭ በመሆኑ ይበልጡን ይጎዳል ብለዋል።

ባለሥልጣኗ ለጸጥታው ምክር ቤት ባደረጉት ገለፃ አስራ ዘጠኝ ሚሊዮን ህዝብ ተርቧል። ከዚያ ውስጥ 16 ሺህ ሰዎች የከበደ የረሃብ ቸነፈር አፋፍ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG