በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተመድ ለሶማሊያው ድርቅ 1 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል አለ


ፋጡማ አብዲ በተመጣጠነ ምግብ እጥረት በሽታ ሁለት ልጆቿን በሞት አጥታለች። ሞቃዲሾ ወጣ ብሎ የሚገኝ መጠለያ ጣቢያ እአአ 9/3/2022
ፋጡማ አብዲ በተመጣጠነ ምግብ እጥረት በሽታ ሁለት ልጆቿን በሞት አጥታለች። ሞቃዲሾ ወጣ ብሎ የሚገኝ መጠለያ ጣቢያ እአአ 9/3/2022

በሚቀጥሉ ወራትና ዓመት መጀመሪያ የሶማሊያውን ረሃብ ለመከላከል ቢያንስ 1 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮችና የአስቸኳይ ዕርዳታ አስተባባሪ (ኦቻ) ሃላፊ ማርትን ግሪፊትስ ተናገሩ፡፡

ኃላፊው ይህን የተናገሩት በአፍሪካ ቀንድ ይከሰታሉ ለተባሉት ሁለት ከፍተኛ የድርቅ ወቅቶች ያስፈልጋል ያሉትን አጣዳፊ የእርዳታ ትንበያ ትናንት ማክሰኞ ባስታውቁበት ወቅት ነው፡፡

ግሪፍትስ በሶማሊያ መዲና ሞቃድሾ ባላፈው ሳምንት ውስጥ በሰጡት መግለጫ የድርቁን ሁኔታ የሚገመግመው ገለልተኛው የባለሙያዎች ቡድን ሶማሊያ ውስጥ ከጥቅምት እስከ ታህሳስ ባለው ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ረሃብ ሊከሰት እንደሚችል ማስታወቁን ተናግረዋል፡፡

ግሪፊትስ "ልናስወግደውና ልንቆጣጠረው ካልቻልን እአአ በ2016 እና 2017 የተከተሰተው ሁኔታ ሊደገም ይችላል" ሲሉም አስጠንቅቀዋል፡፡

በዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የልማትና ተራድኦ ድርጅት የሚዘጋጀው ቅድመ ማስጠንቀቂያ፣ ሰኞ ባወጣው ሪፖርት ረሃቡ በዚህ ዓመት መጨረሻ ላይ ሶማሊያ ውስጥ በሦስት አካባቢዎች ሊከስት እንደሚችል አስታውቋል፡፡

በሌላም በኩል በአፍሪካ ቀንድ እየተባባሰ የመጣውን ድርቅ አስመልክቶ ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ፌዴሬሽን ዛሬ ባወጣው መግለጫ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ሶማሊያውያንና ኬንያውያን ምግብና ውሃ ፍለጋ መሰደዳቸውን አስታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG