በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጸጥታው ምክር ቤት በማሊው ማዕቀብ የምዕራብ አፍሪካ አገሮችን እንዲደግፍ ተጠየቀ


ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀኃፊ አንቶኒዮ ጉዜሬዥ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት በኒው ዮርክ ከተማ፣ እአአ ነሀሴ 16/2021 ንግግር አያደረጉ።
ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀኃፊ አንቶኒዮ ጉዜሬዥ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት በኒው ዮርክ ከተማ፣ እአአ ነሀሴ 16/2021 ንግግር አያደረጉ።

በተባበሩት መንግሥታት ጸጥታው ምክር ቤት ውስጥ ያሉ የአፍሪካ አገሮች የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ ኅብረት አባል አገሮች /ኢኮዋስ/ በዚህ ሳምንት በማሊ ላይ የጣሉትን ማዕቀብ ምክር ቤቱ እንዲደግፈው ጠይቁ፡፡

በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን የጨበጠው የማሊ ወታደራዊ ኃይል፣ ምርጫውንና የሽግግር ጊዜውን በአምስት ዓመት ለማራዘም መወሰኑን በመቃወም፣ ኢኮዋስ ያስተላለፈውን ማዕቀብ የጸጥታው ምክር ቤት እንዲያከብርና እንዲተባበር፣ በምክር ቤቱ የአፍሪካ አባላት መጠየቃቸው ተመልክቷል፡፡

የምዕራብ አፍሪካ አገራት፣ በየብስና በአየር፣ ከማሊ ጋር የሚያገናኛቸውን የንግድ ግንኙነት አቋርጠዋል፡፡

ማሊም ውሳኔውን ካስተላለፉባት አገሮች ጋር ድንበሯን በመዝጋትና አምባሳደሮችዋን በመጥራት አጸፋውን መልሳለች፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 15ሺ የሰላም አስከባሪዎችና ፖሊሶች በአገሪቱ ውስጥ ያሉት ሲሆን የሽግግሩን ጊዜ አስመልከቶ አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጥ አሳስቧል፡፡

በሌላም በኩል የማሊ ወታደራዊ መንግሥት በሩሲያ የሚደገፍ የቅጥር ወታደሮችን ወደ አገሪቱ መጋበዙ በዘገባው ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG