በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተመድ ዋና ጸሃፊ ጠ/ሚ ዐቢይ ከአፍሪካ ህብረት ልዑካን ጋር መወያየታቸውን አደነቁ


ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶንዮ ጉቴሬዥ
ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶንዮ ጉቴሬዥ

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ከአፍሪካ ህብረት ልዩ ልዑካን ጋር መወያየታቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶንዮ ጉቴሬዥ በደስታ ተቀብለዋል።

የዋና ጸሃፊው ቃል አቀባይ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል ጉቴሬዥ የአፍሪካ ህብረት የያዘው ጥረት የመንግሥታቱ ድርጅት ሙሉ ድጋፍ እንዳለው አሳውቀዋል፥ ወገኖቹም ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የቀረበላቸውን ወሳኝ ዕድል እንዲጠቀሙበት ጥሪያቸውን ያቀርባሉ ብለዋል።

ዋና ጸሃፊ ጉቴሬዥ በትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታና ቀጣናዊ አንድምታውን በቅርበት መከታተላቸውን እንደቀጠሉ መሆናቸውንም ቃል አቀባያቸው አክለዋል።

የሲቪሎች ደህንነት መጠበቅ፥ የሰብዓዊ መብቶች መከበር ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች የሰብዓዊ ረድዔት ተደራሽነት መረጋገጥ እንዳለበት አበክረው ያሳሰቡት ዋና ጸሃፊ አንቶንዮ ጉቴሬዥ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እነዚህን ግዴታዎች በታላቅ ትኩረት እንደሚያከብሩ ዛሬ በድጋሚ ማረጋገጣቸው እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል።

XS
SM
MD
LG