በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አይኦኤም ለትግራይ ተፈናቃዮች አስቸኳይ ድጋፍ ተማጸነ


ፎቶ ፋይል፦ የተመድ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች
ፎቶ ፋይል፦ የተመድ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች

ዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት /አይኦኤም/ ትግራይ ውስጥ ለተፈናቃዮች አጣዳፊ መጠለያ ለማቅረብ ሃያ ሰባት ሚሊዮን ዶላር ባስቸኳይ እንደሚያስፈልገው አስታወቀ።

የተመድ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች በትናንት ማክሰኞ ገለፃቸው እንዳስታወቁት በአሁኑ ወቅት ትግራይ ውስጥ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ከ2 ነጥብ 1ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎች የሚገኙ መሆኑን አይኦኤም አስታውቋል።

ግጭቱን ሸሽተው ወደሱዳን የተሰደዱ ያሉ ሲሆን ብዙዎች ግን በክልል ባሉ 116 የተፈናቃዮች መጠለያ ካምፖች የተጠለሉ መሆናቸውን አይኦኤም ማስታወቁን ቃል አቀባዩ ጠቅሰዋል።

አይኦኤም ለተፈናቃዮቹ መጠለያ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ እንደ የብርድ ልብስ እና ምግብ ማብሰያ የመሳሰሉ ቁሳቁስ ለማቅረብ መንግሥታዊ ያልሆኑ ሰላሳ ሶስት የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እንዲሁም ሁለት የተባበሩት መንግሥታት ተቋማትን በመምራት እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ገልጸዋል።

አይኦኤም በሰሜን ኢትዮጵያው ቀውስ ለተጎዱ ሰዎች መርጃ ባለፈው ሃምሌ ወር 63 ነጥብ 4ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ የተማጸነ ሲሆን እስካሁን የደረሰው 28ነጥብ 7ሚሊዮን ዶላር ብቻ መሆኑን የመንግሥታቱ ድርጅት ቃል አቀባይ አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG