በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን የሚሰደዱ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ተመድ አስታወቀ


በኢትዮጵያ ሰሜናዊ ትግራይ ክልል እየተካሄደ ካለው ውጊያ በመሸሽ ወደ ጎረቤት ሃገር ሱዳን የሚጓዙ
በኢትዮጵያ ሰሜናዊ ትግራይ ክልል እየተካሄደ ካለው ውጊያ በመሸሽ ወደ ጎረቤት ሃገር ሱዳን የሚጓዙ

በኢትዮጵያ ሰሜናዊ ትግራይ ክልል እየተካሄደ ካለው ውጊያ በመሸሽ በሚቀጥለው ከስድስት ወር እስከ አንድ ዓመት የሚደርስ ጊዜ ቁጥራቸው ወደሁለት መቶ ሽህ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ወደአጎራባች ሱዳን ሊሰደዱ ይችላሉ የሚል ስጋት እንዳለው ተመድ አስታወቀ።

ባሳለፍነው ረቡዕ 1896 ሰዎች ድንበር አቋርጠው ሱዳን ምግባታቸውን የገለጠው ድርጅቱ ውጊያው ከተቀሰቀሰበት ካለፉት ሁለት ሳምንታት ወዲህ ሱዳን የገቡት ስደተኞች ስላሳ ሦስት ሺህ መድረሳቸውን ተናግሯል።

ብዙዎቹ ሃገር ቤት ከቀረን ውጊያው ውስጥ እንድንሳተፍ ያስገድዱናል ብለው የሰጉ ወጣት ወንዶች መሆናቸውንም ጨምሮ አመልክቷል።

የህጻናት መርጃ ድርጅት /ዩኒሴፍ/ ትናንት ሃሙስ ባወጣው መግለጫው ትግራይ ውስጥ ማኅበረሰቦች ጋ መድረስ የማይቻል መሆንኑና መገናኛዎችም እንደተቋረጡ በመሆኑ ሰብዓዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው 2ነጥብ ሦስት ሚሊዮን ህጻናትን ለመድረስ አልተቻለም ሲል አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG