በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመን ውስጥ 14 ሚሊዮን ህዝብ በቸነፈር ሊመታ ይችላል ሲል ተመድ አስታወቀ

ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የመን ውስጥ ቸነፈሩን እየታገሉ ያሉት የሰብዓዊ ረድዔት ሰራተኝኞች እየተሸነፉ ነው ሲሉ ያስጠነቀቁት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ረድዔት ዋና ኃላፊ አሥራ አራት ሚሊዮን ህዝብ በከባድ ቸነፍር በቅርቡ ሊመታ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል፡፡

የመን ውስጥ ቸነፈሩን እየታገሉ ያሉት የሰብዓዊ ረድዔት ሰራተኝኞች እየተሸነፉ ነው ሲሉ ያስጠነቀቁት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ረድዔት ዋና ኃላፊ አሥራ አራት ሚሊዮን ህዝብ በከባድ ቸነፍር በቅርቡ ሊመታ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል፡፡

ማርክ ሎውኮክ የመንግሥቱ ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት ባደረጉት ገለፃ እጅግ ግዙፍ የሆነ የረሃብ ቸነፈር የመን ላይ አፍጥጦ መጥቷል ብለዋል። የግዝፈቱና የክብደቱም መጠትን ማናቸውም የሰብዓዊ ዕርዳታ ባለሙያ በሥራ ዘመኑ ገጥሞት የማያውቅ እንደሆነ ነው ያስገነዘቡት።

የተመድ ባለሥልጣን የመን ላይ የተደቀነውን አደጋ በተመለከተ ሲያስጠነቅቁ ይሄ የመጀመሪያቸው አይደለም። ባለፈው የአውሮፓውያን ዓመት ሁለት ጊዜ ማስጠቀቂያውን የሰጡ ሲሆን ያኔ የሰብዓዊ ዕርዳታ ምላሹ በከፍተኛ መጠን በማደጉና ሳውዲ ዓረቢያ የምትመራዊ ህብረት የየመን ወደብ ከበባውን በማቆሙ እጅግ ይከፋ የነበረውን ሆኔታ ለመከላከል ተችሏል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG