በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ  የሶሪያ ግጭት እንዲቆም ጥሪ አቀረበ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሶሪያ ውስጥ ግጭት ከ6 ሚሊዮን በላይ ስደተኞችን ጨምሮ ወደ 12 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን አፈናቅሏል ብሏል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሶሪያ ውስጥ ግጭት ከ6 ሚሊዮን በላይ ስደተኞችን ጨምሮ ወደ 12 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን አፈናቅሏል ብሏል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሶሪያ ልዩ መልዕክተኛ፣ ከፕሬዝደንት ባሽር አል አሳድ ሥልጣን መወገድ ተከትሎ ባለፉት ሦስት ወራት ዐዲስ በተቀሰቀሰው ግጭት እየታመሰች ባለችው ሀገር ሁከቱ እንዲቆም ተማጸኑ፡፡ የሰላማዊ ዜጎች ደኅንነት እንዲጠበቅም ጥሪ አቀረቡ፡፡

የመንግሥታቱ ድርጅት ልዩ መልዕክተኛ ጌር ፔደርሰን ጥሪያቸውን ያቀረቡት፣ የዲሞክራሲ ደጋፊዎች ሀገሪቱን ለዐስርት ዓመታት ወደ ዘለቀው የርስ በርስ ጦርነት ያመራው ጸረ አሳድ ተቃውሞ የተጀመረበት 14ኛው ዓመት መታሰቢያ በሆነው በዛሬው ዕለት ነው፡፡

“የለውጥ ጥያቄ ጭካኔ የተሞላበት ከፍተኛ ብጥብጥ ገጥሞታል፣ በዘመናችን እጅግ አሰቃቂ ወደ ኾነ ግጭት አምርቷል” ያሉት ፔደርሰን “ግጭቱ ጥልቅ የሆነውን አስከፊውን የሰው ልጅ ጭካኔ አጋልጧል።” ብለዋል፡፡

“የሚወዷቸውን በሞት ያጡ ቤተሰቦች ሐዘን ላይ ናቸው፡፡ ማኅበረሰቦች ተበታትነዋል፡፡ ሚሊዮኖች ከቀያቸው ተነቅለዋል፣ብዙዎችም የጠፉባትን በማፈላለግ ላይ ይገኛሉ” ሲሉም ፔደርሰን አክለዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሶሪያ ውስጥ ግጭት ከ6 ሚሊዮን በላይ ስደተኞችን ጨምሮ ወደ 12 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን አፈናቅሏል ብሏል።

አሳድ እ.ኤ.አ. ታኅሣሥ 2024 ከሥልጣን ቢወገዱም ከመጋቢት 6 ጀምሮ በጠረፉ ክፍለ ግዛት በኩል በተጀመረ ሁከት ሀገሪቱ በርካቶችን ለሞት በዳረገ ሁከት ተንጣለች፡፡

የቀድሞ ፕሬዝደንት ታማኞች ከጸጥታ ኃይሎች ጋራ ባደረጉት አስከፊ ግጭት በርካታ ሲቪሎችን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሞተዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG