በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጉቴሬዥ በሱዳን ያለው ግጭት እንዲቆም በድጋሚ ጠየቁ


የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ

በሱዳን በሁለቱ የጦር ጀነራሎች መካከል የሚካሔደው ውጊያ፣ ተጨማሪ እልቂት ከማስከተሉና ወደ ቀጣናዊ ግጭት ከመስፋቱ በፊት እንዲቆም፣ በኬንያ የሚገኙት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ ጥሪ አድርገዋል፡፡

ተፋላሚ ኃይሎቹ የሱዳንን ሕዝብ ጥቅም እንዲያስቀድሙ፣ ዋና ጸሐፊው ጥሪ አድርገዋል፡፡ “ሱዳናውያን ሰብአዊ አደጋ ተጋርጦባቸዋል፡፡ ሆስፒታሎች ወድመዋል፤ የርዳታ መጋዘኖች ተዘርፈዋል፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሱዳናውያን ከምግብ ዋስትና አደጋ ጋራ ተፋጠዋል፤” ሲሉ ጉቴሬዥ ለዜና ሰዎች ተናግረዋል፡፡

የሱዳን ተፋላሚ ጄኔራሎች ከሁለት ሳምንት በላይ የቆየውን ውጊያ ማቆም አለባቸው፤ ውጊያው መቆም አለበት፤ አሁኑኑ መቆም አለበት፡፡ ተጨማሪ እልቂት ከማስከተሉ እና ወደ ቀጣናዊ ግጭት ተስፋፍቶ ለዓመታት አካባቢውን ከማወኩ በፊት መቆም አለበት፤”

በመኾኑም፣ “የሱዳን ተፋላሚ ጄኔራሎች ከሁለት ሳምንት በላይ የቆየውን ውጊያ ማቆም አለባቸው፤ ውጊያው መቆም አለበት፤ አሁኑኑ መቆም አለበት፡፡ ተጨማሪ እልቂት ከማስከተሉ እና ወደ ቀጣናዊ ግጭት ተስፋፍቶ ለዓመታት አካባቢውን ከማወኩ በፊት መቆም አለበት፤” ብለዋል ጉተሬዥ፡፡

ዋና ጸሐፊው የአፍሪካ ጉብኝታቸውን ቀጥለው ወደ ቡጁምቡራ - ብሩንዲ በማቅናት፣ በቀጣናው፣ በተለይም በኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ባለው የጸጥታ ኹኔታ ላይ እንደሚወያዩ፣ የቪኦኤዋ ማሪያማ ዲያሎ ከናይሮቢ ከላከችው ዘገባ ለመረዳት ተችሏል፡፡

XS
SM
MD
LG