በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኮንጎ ያገረሸው ግጭት “አሳስቦኛል አለ”


የተመድ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች
የተመድ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች

በኮንኮ ጦር ሰራዊት፣ በኤም-23 ሚሊሻ አባላት እና በሌሎች ታጣቂ ቡድኖች መካከል፣ ከጥቅምት ወር መጀመሪያ አንስቶ፣ በሰሜናዊ ኪቩ ውስጥ፣ በየዕለቱ እየተካሔዱ ያሉት ግጭቶች፣ በዚያች አገር የሚገኘውን የመንግሥታቱን ድርጅት የሰላም አስከባሪ ተልዕኮ እንዳሳሰበው፣ የድርጅት ቃል አቀባይ ተናገሩ።

የዋና ጸሐፊው ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች፣ ትላንት ኒው ዮርክ ላይ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ “በማሲሲ፣ ሩትሹሩ እና ኒራጎንጎ ግዛቶች ውስጥ የተቀሰቀሱት ግጭቶቹ፣ የምሥራቃዊ ኮንጎው ሁከት በከፍተኛ ደረጃ እንደተባባሰ ያመለክታሉ፤” ብለዋል። ከጎማ ወሰን አቅራቢያ ተፈናቃዮች በተጠለሉባቸው አካባቢዎች በሚደረገው የሰብአዊ አቅርቦት ሥራ ላይም፣ “ከፍተኛ ስጋት ደቅነዋል፤” ሲሉ አስረድተዋል።

“በተጨማሪም፣ ለሰላማዊ ዜጎች ጥበቃ፤ የሰላም አስከባሪው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል፣ ወደ ሩትሹሩ አሰማርተዋል፤” ብለዋል ዱጃሪች፡፡ አያይዘውም፣ “ጎማ ላይ ሊቃጡ የሚችሉ ጥቃቶችን ለመከላከል፣ ከኮንጎ ጦር ኃይሎች እና ከክልላዊው የምሥራቅ አፍሪቃ ማኅበረሰብ ኃይሎች ጋራ በቅርበት መሥራታቸውን ቀጥለዋል፤” ሲሉ አስታውቀዋል።

በኪትቻንጋ አቅራቢያ በሚገኙ የሰብአዊ ርዳታ ማከፋፈያ ማዕከላት ላይ፣ የጸጥታ ጥበቃ ኬላዎችን ማቋቋማቸውን የገለጹት የድርጅቱ ቃል አቀባይ፣ የተልዕኮው ማዕከል ከሚገኝበት ሥፍራ ለተጠለሉ 25ሺሕ ለሚደርሱ ሰብአዊ ጥበቃ ለሚሹ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች፣ ምግብ ነክ ያልኾኑ ቁሳቁሶች እና ሌሎች የርዳታ አቅርቦቶች በሚሰራጩበትም ወቅት አስፈላጊውን ጥበቃ እንደሚያደርጉ አመልክተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG