በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩክሬናውያን ከሞስኮ ለመራቅ ገናን ዛሬ እያከበሩ ነው


ዩክሬናውያን የኦርቶዶክ ክርስትና ሐይማኖት ተከታዮች  ለመጀመሪያ ጊዜ በዓሉን ዛሬ በፈረንጆች የገና ቀን በማክበር ላይ ናቸው፤ ኬየቩ፣ ዩክሬን
ዩክሬናውያን የኦርቶዶክ ክርስትና ሐይማኖት ተከታዮች  ለመጀመሪያ ጊዜ በዓሉን ዛሬ በፈረንጆች የገና ቀን በማክበር ላይ ናቸው፤ ኬየቩ፣ ዩክሬን

የገና በዓልን ታህሳስ 29 ቀን ሲያከብሩ የኖሩት ዩክሬናውያን የኦርቶዶክ ክርስትና ሐይማኖት ተከታዮች ለመጀመሪያ ጊዜ በዓሉን ዛሬ በፈረንጆች የገና ቀን በማክበር ላይ ናቸው፡፡ ይህ የሆነው መንግሥታቸው በሩሲያ ላይ ቁጣ ለመግለፅ የበዓሉን ቀን በመቀየሩ ነው።

የዛሬውን የፈረንጆች የገና በዓል አስመልክተው ትናንት በዋዜማው መልዕክት ያስተላለፉት ፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ፣ "ሁላችንም ዩክሬናውያን አንድ ላይ ነን ፡፡ የገናን በዓል፣ በአንድ ቀን፣ እንደ አንድ ትልቅ ቤተሰብ፣ እንደ አንድ ሕዝብ በአንድነት አብረን እናከብረዋለን" ብለዋል።

ሁላችንም ዩክሬናውያን አንድ ላይ ነን ፡፡  የገናን በዓል፣ በአንድ ቀን፣ እንደ አንድ ትልቅ ቤተሰብ፣ እንደ አንድ ሕዝብ በአንድነት አብረን እናከብረዋለን"

በደቡባዊው ጥቁር ባህር ወደብ በሚገኘው እና ባጌጡ የጥድ ዛፎች በተዋበው ቤተክርስቲያን፣ ቄሶች በወርቅ ያቄጡ መጎናፀፊያዎች ለብሰው የገና ዋዜማን በፀሎት የመሩ ሲሆን፣ ምዕመናን ሻማ በማብራት ስርዓቱን ተካፍለዋል።

ኦሌና የተባለ፣ ልጁ በዩክሬን ጦር ውስጥ የህክምና አገልግሎት የሚሰጥ አንድ ምዕመን "ገናን ከሞስኮ ርቀን ከመላው ዓለም ጋር ማክበር እንዳለብን እናምናለን። ያንን ነው ልናስተላልፍ የምንፈልገው መልዕክት" ሲል ለአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ተናግሯል።

ዘለንስኪ የገና በዓል እ አ አእ ታሕሳስ 25 እንዲከበር የሚያዘውን አዲሱን ህግ ሐምሌ ላይ የፈረሙት፣ “ዩክሬናውያን ገናን አንደኢትዮጲያ አቆጣጣር በታህሳስ 29 እንዲያከብሩ ካደረጋቸው የሩሲያ ጫና እንዲላቀቁ እድል ይሰጣቸዋል” በማለት ነው። የዩክሬን ካቶሊክ ቤተክርስቲያንም በዛሬው እአእ በታህሳስ 25 ለማክበር ተስማምቷል። በዩክሬን የሩሲያ እና የሶቪየትን አሻራ ለማስወገድ እየተወሰዱ ካሉ እርምጃዎች መከከል፣ ገና የሚከበርበትን ቀን ከመለወጥ በተጨማሪ፣ የመንገዶችን ስያሜ መቀየር እና ሐውልቶችን ማስወገድ ይገኙበታል።

በታሪክ ከሩሲያ ጋር ትስስር ያላቸው አንዳንድ የዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናት ግን በጦርነቱ ምክንያት ከሩሲያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዳቋረጡ ቢገልፁም፣ የገና በዓልን በታህሳስ 29 ማክበራቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG