በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜለነስኪ ዩክሬን 70 የሩሲያ ሚሳዬሎችን መትታ መጣሏን ተናገሩ


ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ
ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ

ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ ዩክሬን 70 የሚደርሱ የሩሲያ ሚሳዬሎችን መትታ መጣሏን ተናገሩ፡፡

ዜለነስኪ ይህን የተናገሩት ሩሲያ ዩክሬን ላይ ዛሬ ማክሰኞ ታህሳስ 23 2016 ከፍተኛ የአየር ጥቃት ካደረሰች በኋላ ነው፡፡ሀገራቸው ለሩሲያው ጥቃት ምላሽ እንደምትሰጥ የተናገሩት ዜሌነስኪ "ሩሲያ ለተነጠቀው ህይወት ሁሉ ምላሽ ትሰጣለች" ብለዋል።

ዜለንስኪ በመልዕክት መቀባበያው ቴሌግራም ላይ ባወጡት የቪዲዮ መልዕክት ሩሲያ በቅርቡ ባደረገችው ጥቃት ወደ 100 የሚጠጉ የተለያዩ ዓይነት ሚሳዬሎችን መተኮሷን ገልጸዋል።

ከዚያ ውስጥ “ቢያንስ 70 ሚሳዬሎች ተመትተው ወድቀዋል፡፡ 60 ያህሉ በኪቭ ግዛት ነበሩ፡፡ ካኸርኪቭም እንዲሁ ክፉኛ ተመታለች” ሲሉ ዜለነስኪ ተናግረዋል፡፡

የዩክሬን ጦር አዛዥ ዛሬ ማክሰኞ እንደተናገሩት፣ የአየር መካከላከያው በሩሲያ የተተኮሱ 10 የኪንዛል ፣ 59 የክሩዝ እና ሶስት የካሊብር ሚሳዬሎችን መጥቶ ጥሏል፡፡

በሩሲያው የአየር ጥቃት ቢያንስ ሁለት ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች መቁሰላቸው ተጠቅሷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG