በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ ኦዴሳን በሚሳዬል መታች

የሩሲያ ሚሳዬል የዩክሬንን የወደብ ከተማ ኦዴሳ መምታቱን ተከትሎ፣ አንድ ጥንታዊ ሕንጻ በእሳት ተያይዟል።
የሩሲያ ሚሳዬል የዩክሬንን የወደብ ከተማ ኦዴሳ መምታቱን ተከትሎ፣ አንድ ጥንታዊ ሕንጻ በእሳት ተያይዟል።

የሩሲያ ሚሳዬል የዩክሬንን የወደብ ከተማ ኦዴሳ መምታቱን ተከትሎ፣ አንድ ጥንታዊ ሕንጻ በእሳት ተያይዟል።

በሚሳዬል ጥቃቱ አራት ሰዎች እንደሞቱ የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል።

የጥቃት ማስጠንቀቂያው ለጥቂት ደቂቃዎች ብቻ የተሰጠ በመሆኑ፣ በመንገድ ላይ የነበሩ ሰዎች ለመደበቅ በቂ ጊዜ እንዳልነበራቸው ታውቋል።

“የሃሪ ፖተር ግንብ” በመባል በአካባቢው ሰዎች የሚጠራው ሕንጻ ክፉኛ ተመቶ በእሳት ተያይዟል።

ሕንጻውን እና በአካባቢው ያሉ ሌሎች ንብረቶች በባለቤትነት የያዘ ግለሰብ በአደጋው ሕይወቱ ማለፉም ታውቋል።

በሚሳዬል ጥቃቱ ወቅት የባሕር ዳርቻው መዝናናዎች፣ በእግር መንሸራሸሪያ መንገዶች እና ፓርኮች በሰዎች ተሞልተው እንደነበርም ታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG