በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩክሬን የጤና ተቋማት ላይ የደረሱትን ጥቃቶች የተመድ መስሪያ ቤቶች አወገዙ


በሳልቲቫካ የህክምና ሥፍራ በዩኒሴፍ ጊዜያዊ የወሊድ ማዕከል፣ ምድር ቤት ውስጥ ካርኪቭ፣ ዩክሬን እአአ የካቲት 28/2022
በሳልቲቫካ የህክምና ሥፍራ በዩኒሴፍ ጊዜያዊ የወሊድ ማዕከል፣ ምድር ቤት ውስጥ ካርኪቭ፣ ዩክሬን እአአ የካቲት 28/2022

ዩክሬኑ ጦርነት በአስቸኳይ ተኩስ አቁም እንዲደረግ እና በጤና ተቋማት እና ሰራተኞች ላይ ጥቃት እንዳይፈጸም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መሥሪያ ቤቶች ትናንት ዕሁድ ተማፅኖ አቀረቡ። እንዲህ ያለው አድራጎት ምንም ምክንያት የማይሰጠው የክፋት ድርጊት ነው ሲሉም ገልጸውታል።

ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ በጤና ጥበቃ ተቋማት ላይ ሰላሳ አንድ ጥቃቶች መፈጸማቸውን ዩኒሴፍ የሥነ ህዝብ ተቋሙ እና የዓለም የጤና ድርጅት በጋራ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ህፃናትን፣ ህሙማንን እና ነፍሰ ጡሮችን እንዲሁም ራሳቸውን ለአደጋ አጋልጠው የሌሎችን ህይወት ለማትረፍ የሚሰሩ የጤና ሰራተኞችን ማጥቃት እጅግ አረመኒያዊ አድራጎት ነው፣ በአስቸኳይ ተኩስ አቁም መደረግ አለበት ሲሉ አሳስበዋል።

XS
SM
MD
LG