የዩክሬን ኃይሎች ዛሬ ማክሰኞ በክራይሚያ የሚገኘውን የሩስያ የባህር ኃይል ማረፊያ መርከብ በመምታት በሩሲያ ጥቁር ባህር መርከቦች ላይ ሌላ ጉዳት አድርሰዋል።
ጥቃቱ የተፈጸመው ሩሲያ በኃይል ወደሯሷ በቀላቀለቻት ክሪሚያ ውስጥ በምትገኘው የፊዮዶሲያ ወደብ መሆኑም ተገልጿል።
የዩክሬን አየር ኃይል ግዙፉ የመርከብ ማሳረፊያ ኖቮቸርካስክን ያወደመው ክሩዝ ሚሳኤሎችን ተጠቅሞ እንደሆነ አስታውቋል፡፡
የዩክሬን አየር ሃይል እዝ ቃል አቀባይ ዩሪ ኢህናት ለቪኦኤ እንደተናገሩት፣ የዩክሬን ጦር ስለ መርከቧ ቦታ እና ጭነት እንዲሁም ክልሉን ስለሚጠብቁት የሩሲያ አየር መከላከያዎች መረጃ እንደነበረው ተናግረዋል።
ቀስ በቀስ የጥቁር ባህር መርከቦችን እና በጥቁር ባህር ላይ ያላትን ተጽእኖ እያጣች ነው"
ቃል አቀባዩ የዩክሬን ጦር ኢላማዎችን በትክክል የሚመቱ ጥቃቶችን በማድረስ የተሻለ እየሆነች ነው ብለዋል፡፡
ሩሲያ "ቀስ በቀስ የጥቁር ባህር መርከቦችን እና በጥቁር ባህር ላይ ያላትን ተጽእኖ እያጣች ነው" ሲልኩም ቃል አቀባዩ አክለው ተናግረዋል፡፡
የሩሲያ ዜና ወኪሎች ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ስለጥቃቱ ማብራሪያ እንደተሰጣቸው ዘግበዋል፡፡
የሩሲያ መካላከያ ሚኒስቴርም የዩክሬናውያኑ ጥቃት በፊዮዶሲያ የባህር ኃይል ወደብ የምትገኘውን ኖቮቸርካስክ ላይ ጉዳት ማድረሱን አስታውቋል፡፡
መድረክ / ፎረም