በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩክሬን የሩሲያ ነዳጅ ማጣሪያዎችን በድሮን ማጥቃት መጀመሯን አስታወቀች


FILE - A Ukrainian serviceman operates a drone on the front line in Zaporizhzhia region, Ukraine, June 14, 2024.
FILE - A Ukrainian serviceman operates a drone on the front line in Zaporizhzhia region, Ukraine, June 14, 2024.

ዩክሬን ዛሬ ዐርብ በደቡባዊ ሩሲያ በሚገኙ በርካታ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካዎች እና ወታደራዊ ማዕከላት ላይ በሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮኖች) ጥቃት ማድረሷን አስታወቀች።

ሞስኮ በጥቃቱ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን እና 114 ድሮኖችን ከጥቅም ውጭ ማድረጓን ተናግራለች።

ኪቭ የሞስኮን ወታደራዊ ኃይል የሚያጠናክሩ በመሆናቸው ፍትሃዊ ኢላማዎች ናቸው ያላቻቸውን በሩሲያ ውስጥ የሚገኙ የነዳጅ ፋብሪካዎች ላይ በቅርብ ወራት ውስጥ በርካታ ጥቃቶችን ፈጽማለች።

ሩሲያም እንዲሁ በዩክሬን የኃይል ማመንጫዎች ላይ በደርዘን የሚቆጠሩ አውዳሚ ጥቃቶችን መሰንዘር ጀምራለች።

የኪቭ ጦር ሰው አልባ አውሮፕላን (ድኖሮኖቹን) አፊፕስኪ፣ ኢልስኪ፣ ክራስኖዳር እና አስትራካን በተባሉ የዘይት ማጣሪያዎች እና በደቡብ ሩሲያ በሚገኝ የሬዲዮ እና የስለላ ማዕከል ላይ ማሰማራቱን አስታውቋል።

ጥቃቶቹ በክራስኖዶር የድሮን ዝግጅት እና ማከማቻ ቦታ ላይ ያነጣጠሩ ሲሆን ጥቃቶቹን ተከትሎ ተከታታይ ፍንዳታ እና የእሳት አደጋ መድረሱን የዩክሬን መከላከያ ገልጿል።

በሞስኮ የሚገኘው የመከላከያ ሚኒስቴር “የሩሲያ ፀረ-አየር መከላከያ መሳሪያዎች በክራይሚያ እና በጥቁር ባህር ላይ 70 ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ፣ በክራስኖዳር ክልል 43 ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እና በቮልጎግራድ ላይ አንድ ሰው አልባ አውሮፕላን ደምስሰዋል” ብሏል።

ከሁለት ዓመታት በላይ የሩስያን ወታደራዊ ጥቃት ስትዋጋ የቆየችው ዩክሬን ከቅርብ ወራት ወዲህ በሩሲያ ግዛት ላይ የምታደርገውን ጥቃት በማጠናከር የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎችን በማጥቃት ላይ ነች።

የሩስያ ሚሳዬል እና ድሮን በዩክሬን የኃይል መሠረተ ልማት ላይ ባደረሷቸው ጥቃቶች የሀገሪቱን ሃይል የማመንጨት አቅም በማዳከሙ ኪቭ የኤሌክትሪክ ኃይል ከአውሮፓ ኅብረት እንድታስገባ አስገድዷታል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG