በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩክሬን 18 የሩስያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ማውደሟን አስታወቀች


የድንገተኛ ጊዜ ሰራተኞች የሩስያ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት በደረሰበት ቦታ ኦዴሳ፣ ዩክሬን እአአ መጋቢት 5 ቀን 2024
የድንገተኛ ጊዜ ሰራተኞች የሩስያ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት በደረሰበት ቦታ ኦዴሳ፣ ዩክሬን እአአ መጋቢት 5 ቀን 2024

ሩስያ ሌሊቱን በሰነዘረችው የዓየር ጥቃት ያሰማራቻቸውን 18 ሰው አልባ የውጊያ አውሮፕላኖች ማውደሟን ዩክሬን አስታወቀች። በተጨማሪም ከክራይሚያ ባሕረ ገብ መሬት አቅራቢያ የነበረን አንድ የሩስያ ወታደራዊ ቃኝ የጦር መርከብ ባህር ኃይሉ እና ሰው አልባ የውጊያ አውሮፕላኖች መመታታቸውን የዩክሬን ጦር የአየር መከላከያ አስታውቋል።

ሩስያ በአንድ ሌሊት በድምሩ 22 ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ስታሰማራ፤ ከእነኚህም ውስጥ 18ቱ በኦዴሳ ሰማይ ላይ ተመተው መውደቃቸውን የዩክሬን አየር ሃይል አስታውቋል። በሩስያ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት አንድ የመዝናኛ ሥፍራን ጨምሮ በበርካታ ሕንፃዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ያስታወቁት የኦዴሳ አገረ ገዥ ኦሌህ ኪፐር በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት ግን ያለመኖሩን ተናግረዋል።

የዩክሬን ወታደራዊ መረጃ አክሎም፣ የተመታቸው የሩስያ የጦር መርከብ ሰርጌይ ኮቶቭ የተባለችው መሆኗን ገልጾ “የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች የከርች ባሕር ዳርቻን በመደብደብ በወደቡ ላይም ጉዳት አድርሰዋል" ብሏል። ጥቃቱ በሩስያው ጥቁር ባህር አካባቢ የሚገኙ የጦር መርከቦችን ዒላማ ካደረጉ የዩክሬይን ወታደራዊ እርምጃች የቅርብ ጊዜ መሆኑ ነው።

ሩስያ ለሊቱን የፈጸመችውን ጥቃት ተከትሎ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ባሰሙት ንግግር፣ የዩክሬን ባለሥልጣናት የሞስኮን "ቀጣይ እቅዶች" እንደሚያውቁ እና አገራቸው ወታደራዊ ምላሽ መስጠቷን እንደምትቀጥል ተናግረዋል። ዘለንስኪ ይህን ያሉት ከከፍተኛ ወታደራዊ እና የደህንነት ባለሥልጣናት ጋራ ያደረጓቸውን ተከታታይ ስብሰባዎች አስመልክቶ በተናገሩበት ወቅት ነው።

በተያያዘም የዩክሬኑ መከላከያ ሚንስትር ሩስቴም ኡሜሮቭ ውጊያውን አስመልክቶ ስላለው ተጨባጭ ሁኔታ በትናንትናው ዕለት ከዩናይትድ ስቴትሱ አቻቸው ሎይድ ኦስቲን ጋር በስልክ ተነጋግረዋል። በንግግራቸውም ወቅት ኦስቲን ዩናይትድ ስቴትስ እና አጋሮቿ ለዩክሬይን የሚሰጡትን ድጋፍ ቀጣይነት ማረጋገጣቸውን ፔንታገን በመግለጫው አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG