በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩክሬን የተኩስ አቁም ጠየቀች


የዩክሬን የልዑካን ቡድን የሩሲያ ተወካዮች ጋር ለመነጋገር በጎሜል ክልል ቤላሩስ እአአ ጥር 20/2022
የዩክሬን የልዑካን ቡድን የሩሲያ ተወካዮች ጋር ለመነጋገር በጎሜል ክልል ቤላሩስ እአአ ጥር 20/2022

ዩክሬን በአስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲካሄድና የሩሲያ ኃይሎች በሙሉ ከዩክሬን እንዲወጡ ዛሬ ከሩሲያ ጋር ለመደራደር የሄዱ መልዕከተኞቿ ጠይቀዋል፡፡

በዩክሬንና በሩሲያ መካከል የሚደረገው ድርድር በዩክሬንና ቤላሩስ ድንበር አቅራቢያ እየተካሄደ ሲሆን የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘለነስኪም የሩሲያ ወታደሮች ትጥቃቸውን እንዲያወርዱ ጠይቀዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ዘለነስኪ አውሮፓ አገራቸውን በአስቸኳይ የአውሮፓ ህብረት አባል አድርገው እንዲቀበላትም አሳስበዋል፡፡

ዘለነስኪ ለአውሮፓ ህብረት ባስተላለፉት የቪዲዮ መልዕክታቸው “የኛ ግብ ከሁሉም አውሮፓውያን ጋር አብረን ለመሆን ከሁሉም በላይ ደግሞ ሁላችንም በእኩል ዐይን እንድታይ ያስፈልጋል፣ እርግጠኛ ይህ ፍትሃዊ ነው ደግሞም ይቻላል ብለዋል፡፡”

የኔቶዋና ጸሀፊ ጄን ስቶልትነበርግ ከዩክሬኑ መሪ ጋር በስልክ የተነጋገሩ ሲሆን የዩክሬን ህዝብና የዩክሬን ኃይሎች ስለአሳዩት ጀግንነትና ተጋድሎ አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡

ዋናጸሀፊው በአስተላለፉት የትዊት መልዕክትም “የኔቶ አጋሮች ለዩክሬን የሚሰጡትን የአየር መከላከያ ሚሳዬሎች፣ የጸረ ታንክ መሳሪያች እና እንዲሁም የገንዘብና የሰብአዊ እርዳታዎችን አጠናክረው በመለገስ ላይ ይገኛሉ” ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG