በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከሩስያ ጋር ፍጥጫ በተገባበት የዩክሬይን ክልል የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጁ ፀደቀ


የዩክሬይን ፕሬዚዳንት ፔትሮ ፖሮሼንኮ፣ ከሩስያ ጋር ፍጥጫ በተገባበት የዩክሬይን ክልል ላይ የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ እንዲጣል ያቀረቡትን ጥያቄ፣ ምክር ቤቱ አፀደቀው።

የዩክሬይን ፕሬዚዳንት ፔትሮ ፖሮሼንኮ፣ ከሩስያ ጋር ፍጥጫ በተገባበት የዩክሬይን ክልል ላይ የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ እንዲጣል ያቀረቡትን ጥያቄ፣ ምክር ቤቱ አፀደቀው። ይህ የሆነው፤ ሩስያ ሦስት የዩክሬይንን መርከቦችና ሠራተኞቻቸውን ጥቁር ባህር ላይ ማገቷን ተከትሎ ነው።

ዓዋጁ የተጣለው፣ ከሀገሪቱ 27 ክልሎች በአሥሩ ላይ ሲሆን፣ ተግባራዊነቱም ከነገ ረቡዕ ጀምሮ የፀና ይሆናል።

በሞስኮና በኪዪቭ መካከል ቀውስ ከተፈጠረበት እአአ ከ2014 ዓ.ም ወዲህ፣ የዩክሬይን መንግሥት ይህን ዓይነት ዕርምጃ ሲወስድ የአሁኑ የመጀመሪያ መሆኑ ነው።

ፕሬዚደንት ፖሮሼንኮ ሲናገሩ፣ ዓዋጁ የዩክሬይንን የመከላከያ አቅም ያጠናክራል ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG