በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ኪንግደም በሦስት አዳጊ  ልጃገረዶች ግድያ የተወነጀለ ወጣት በ52 ዓመት እስራት ቀጣች


ተጠርጣሪውን አክሴል ሩዳኩባናን እንደያዘ የሚታመን የእስር ቤት መኪና ፍርድ ቤት ታጅቦ ሲደርስ፤ እአአ ጥር 20/2025
ተጠርጣሪውን አክሴል ሩዳኩባናን እንደያዘ የሚታመን የእስር ቤት መኪና ፍርድ ቤት ታጅቦ ሲደርስ፤ እአአ ጥር 20/2025

በአሜሪካዊቱ የሙዚቃ አቀንቃኝ የቴይለር ስዊፍት ስልት ዳንስ ሥልጠና ዝግጅት ላይ ሦስት ታዳጊ ልጃገረዶችን ሕይወት ያጠፋው እንግሊዛዊ ታዳጊ በዛሬው ዕለት የ52 ዓመታት እስራት ተፈረደበት። ወንጀለኛው አዳጊ የፈጸመው ጭካኔ የተመላ አገዳደል መሆኑን የተናገሩ የአቃቤ ሕግ ጠበቆች የአንደኛዋን ሰለባውን አካል በአሰቃቂ መንገድ መቆራረጡን አመልተዋል።

አክሴል ሩዳኩባና የተባለው የ18 ታዳጊ ባለፈው ሀምሌ ወር በሰሜናዊ እንግሊዝ በምትገኘው ሳውዝፖርት ከተማ ግድያውን መፈጸሙን ባለፈው ሰኞ በሰጠው የእምነት ክህደት ቃል አምኗል። ጥቃቱን ተከትሎም በሀገሪቱ ዙሪያ ከፍተኛ ብጥብጥ መቀስቀሱ አይዘነጋም።

የበጋ ዕረፍት ዝግጅቱ ላይ ከተሳተፉት 26 ልጆች መካከል የነበሩት የስድስት ዓመቷ ቤብ ኪንግ፡ የሰባት ዓመቷ ኤልሲ ዶት ስታንኮምብ እና የዘጠኝ ዓመቷን አሊስ ዳሲልቫ አጉያርን በመግደል የተፈረደበት ሩዳኩምባና ቀሪ ዕድሜውን በወህኒ ቤት ማሳለፍ የሚቀርለት አይመስልም ተብሏል፡፡ ግለሰቡ በተመሰረቱበት አስር የግድያ ሙከራ እና ራይሲን የተባለ ገዳይ መርዝ በመስራት የአእልቃይዳ የስልጠና ወረቀቶች ይዞ መገኘት በሚሉት ወንጀሎች ጥፋተኛ መሆኑን አምኗል፡፡

ሩዳኩባና ወንጀሉን በፈጸመበት ጊዜ 17 ዓመቱ ስለነበረ ያለአመክሮ የዕድሜ ልክ እስራት ሊፈርዱበት እንዳልቻሉ የገለጹት ዳኛው ሆኖም ዕድሜውን ሙሉ ወህኒ ቤት ማሳለፉ አይቀርም ብለዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG