በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እንግሊዝ ውስጥ አንድ ታማሚ ለ505 ቀናት የኮቪድን ቫይረስ በሰውነቱ ይዟል


በብሪታኒያ የሰውነት የመከላከል አቅሙ ክፉኛ የተዳከመ አንድ ታማሚ፣ በሰውነቱ ውስጥ የኮቪድ 19 ቫይረስን አንድ ዓመት ተኩል፣ ወይም 505 ቀናት ይዞ መቆየቱን ሳይንቲስቶች አስታወቁ፡፡

የአሶሼይትድ ፕሬስ ዘገባ እንዳመለከተው ብዙ ሰዎች በየጊዜው ምርመራ የማያደርጉ በመሆኑን በሰውነታቸው ውስጥ ቫይረሱን ይዘው መቆየት የሚችሉ ቢሆንም ለ505 ቀናት ይዞ መቆየት በረጅም ጊዜነቱ ሊመዘግብ እንደሚችል ሳይንቲስቶቹ ገልጸዋል፡፡

የዚህ ግኝት ፍሬ ነገር ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ የሆኑ ሰዎችን ከቫይረሱ መታደግ ሊሰመርበት የሚገባ ጉዳይ መሆኑ እንደሆነ ተመልክቷል፡፡

የዓለም ተማራማሪዎች በዚህ ሳምንት ረጅም ጊዜ ስለሚቆዩት የተላላፊ ቫይረስ በሽታዎች ለመምከር በዚህ ሳምንት በፖርቱጋል እንደሚገናኙ ተነገሯል፡፡

XS
SM
MD
LG