በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሪታንያ የኮቪድ 19 እርዳታን ወደ አፍሪቃ ማብረር ጀመረች


Africa map
Africa map

የብሪታንያ የሮያል አየር ሃይል በገለጸው መሰረት የኮሮናቫይረስ መዛመትን ለመከላከል የሚያስፍልግ አርዳታ የጫነ የመጀመርያ ዙር በረራ ለማድረግ ወደ ጋና ማምራቱን አሶሼትድ ፕረስ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።

የአየር ሃይሉ አይሮፕላን ወደ ጋና ያመራው ወደ 100 የሚጠጉ ሰዎችን ለሚይዝ መስክ ላይ ሊሰራ ለሚችል ሆስፒታል የሚያስፍልጉ ቁሶች ጭኖ መሆኑ ተገልጿል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአይሮፕላን የሚደርስ እርዳታ እንዲደርግ ያቀረበውን ጥሪ የሰሜን አታላንቲክ ቃል ኪዳን ሃገሮች ድርጅት ኔቶ ከደገፈ ወዲህ እርዳታውን በአይሮፕላን ለመላክ ብሪታንያ ቀዳሚዋ ሀገር ሆናለች ሲሉ የኔቶ ዋና ጸሃፊ የንስ ስቶልተንበርግ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

የአለም አቀፉ ወረሽኝ ባስከተለው የጉዞ እገዳ ምክንያት ወደ አፍሪቃ የሚደርጉ በረራዎችን በእጅጉ ጎድቷል። የህክምና አቅርቦትን የመሳሰሉት አፍሪቃ መደረስ ያላባቸው ጭነቶችንም ገድቧል።

ወደ አክራ ጋና የሚላከውን የመስክ ሆስፒታል ለመስራት የሚያስፈልገውን አቅርቦት የማድረሱን ተግባር ለማጠናቀቅ እስከ አምስት የበረራዎች ዙር እንደሚያስፈልግ ብሪታንያ ገልጻለች።

XS
SM
MD
LG