በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እንግሊዝ በሶማሊያ ለተሰማራው ልዑክ ተጨማሪ ገንዘብ መደበች

እንግሊዝ በሶማሊያ ለተሰማራው የአፍሪካ ኅብረት የሽግግር ልዑክ ተጨማሪ 10 ሚሊዮን ዶላር መመደቧን አስታውቃለች፡፡
እንግሊዝ በሶማሊያ ለተሰማራው የአፍሪካ ኅብረት የሽግግር ልዑክ ተጨማሪ 10 ሚሊዮን ዶላር መመደቧን አስታውቃለች፡፡

እንግሊዝ በሶማሊያ ለተሰማራው የአፍሪካ ኅብረት የሽግግር ልዑክ ተጨማሪ 10 ሚሊዮን ዶላር መመደቧን አስታውቃለች፡፡

የእንግሊዝ መንግሥት ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ ተጨማሪ ድጋፉ ባለፉት ሦስት ዓመታት ለአትሚስ እና አሚሶም የተሰጠውን ገንዘብ መጠን 100 ሚሊዮን ዶላር ያደርሰዋል።

“አትሚስ የሶማሊያን ፀጥታ፣ ቁልፍ ሥፍራዎችንና የአቅርቦት ሰንሰለቶችን እንዲሁም መሠረት ልማቶችን በማስጠበቅ ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታል” ብሏል የእንግሊዝ መንግሥት በመግለጫው።

“የሶማሊያ ብሔራዊ ሠራዊት ከሌሎች ጋራ በመተባበር ለሚያካሂደው ዘመቻ፣ የሰብዓዊ ዕርዳታን ለማሳለጥ፣ ምርጫና የፖለቲካ ሂደቶችን በሰላም እንዲከናወኑ ለማስቻል የሚደረገውን ጥረት የእንግሊዝ መንግሥት መደገፉን ይቀጥላል” ሲል አክሏል መግለጫው።

ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ጂቡቲ፣ ዩጋንዳ፣ እና ቡሩንዲ በሶማሊያ ለተሰማራው የኅብረቱ ልዑክ ወታደሮቻቸውን አሰማርተዋል።

‘የአፍሪካ ኅብረት የድጋፍና የማረጋጋት ልዑክ የተሰኘ አዲስ ኃይል በመጪው ጥር ሥራውን ከአትሚስ እንደሚረከብ ይጠበቃል፡፡

ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋራ የተፈራረመችውን የመግባቢያ ሥምምነት ተከትሎ በተነሳው ቅሬታ ምክንያት በአዲሱ ልዑክ ውስጥ ኢትዮጵያ እንድትሳተፍ እንደማትፈልግ ሶማሊያ አስታውቃለች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG