በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለዩጋንዳ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻ ተጀምሯል


በዩጋንዳ በሚመጣው ጥር ወር ለሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የሚወዳደሩት ዕጩዎች የምረጡን ቅስቀሳ ዘመቻ ተጀምሯል።

ይሁን እንጂ የምርጫ ዘመቻዎቹ የኮሮናቫይረስ መዛመትን ለመቆጣጠር የወጡ መመሪያዎችን ሥራ ላይ የማዋል ችግር ላይ እንዳሉ ይስተዋላል፤ በሀገሪቱ በቫይረሱ የሚያዙት ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው።

እአአ ጥር 14 የሚካሄደው ምርጫ የዕጩዎች ቅስቀሳ ከአሁኑ ተጠናክሯል፤ እንቅስቃሴዎ ሲታይ ታዲያ ኮቪድ-19 ወረርሽኝን ያለ እንደማይመስል የቪኦኤ ዘጋቢ ከካምፓላ ትዝብቷን አጋርታለች።

አብዛኞች የቅስቀሳ ዘመቻ ዝግጅቶች ላይ የሚገኙ ደጋፊዎች ማህበራዊ መሰባሰቦችንም ይሁን አፍና አፍንጫ በጭንብል መሸፈንን ችላ እያሉ ናቸው።

የምርጫ አስፈጻሚ ባለሥልጣናቱ በበኩላቸው፣ ዕጩ ተፎካካሪዎቹን በዚህ ጉዳይ ለደጋፊዎቻቸው አርአያ ሆነው ቫይረሱን እንዲከላከሉ እንዲያበረታቱዋቸው እየተማጸኑ ናቸው።

XS
SM
MD
LG