ዋሺንግተን ዲሲ —
ብሄራዊ ንቅናቄ ፓርቲው የሰባ አራት ዓመቱ ሙሴቬኒ ዕጩው እንዲሆኑ የመረጣቸው ካቻምና የሀገሪቱ ፓርላማ ሰባ አምስት ዓመት የነበረው የፕሬዚዳንት የዕድሜ ገደብ እንዲሰረዝ ከወሰነ እና ውሳኔውን ህገ መንግሥታዊው ፍርድ ቤት ባለፈው ሃምሌ ካፀደቀው በኋላ ነው።
የገዢው ፓርቲ ተወካዮች የሚበዙበት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሙሴቬኒ ሥልጣን ላይ የሚቅዩበትን ጊዜ ለማራዘም ሁለት ጊዜ ህገ መንግሥታዊ ለውጥ አድርጓል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ