በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሴት ሾፌሮችን ብቻ የሚቀጥረው የታክሲ አገልግሎት በኡጋንዳ


ፎቶ ፋይል፦ ዲቫ ታክሲ የተባለው የታክሲ አገልግሎት ተቋም ተጠሪ የሴት ሾፌሮችን እያሰለጠኑ
ፎቶ ፋይል፦ ዲቫ ታክሲ የተባለው የታክሲ አገልግሎት ተቋም ተጠሪ የሴት ሾፌሮችን እያሰለጠኑ

ኡጋንዳ ውስጥ ዲቫ ታክሲ የተባለው የታክሲ አገልግሎት፣ ሴት ነጂዎችን ብቻ እንደሚቀጥር ታውቋል። እንዲህ ዓይነቱን የታክሲ አገልግሎት ያፈለቁት፣ የኮሮናቫይረስ መዛመት ሲጀመር፣ የሎጂስቲክስ ሥራቸውን ያጡ ሴት መሆናቸው ታውቋል።

በአሁኑ ወቅት የኮሌጅ ተማሪዎችና መኪኖቻችውን ጥቅም ላይ ለማዋል የሚፈልጉ እናቶች የሚገኙባቸው፣ 70 ሴቶች እንደተስማሩበት ተገልጿል።

የእንዲህ ዓይነቱን የታክሲ አገልግሎት መስራች፣ በአሁኑ ወቅት በኮሮናቫይረስ ምክንያት ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሥራ አጥ ሴቶች መኖራቸውን ገልጸዋል።

ዓለማቀፍ የሰራተኞች ድርጅት እንደሚለው፣ በቫይረሱ ምክንያት በታዳጊ ሃገሮች በተከሰተው የሥራ አጥነት ሁኔታ ክፉኛ የተጎዱት፣ ከወንዶች ይልቅ ሴቶች ናቸው።

XS
SM
MD
LG