በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዑጋንዳ በጫጉላ ሽርሽር ላይ የነበሩ ጥንዶችን የገደሉትን እያደነች ነው


የዑጋንዳ ካርታ
የዑጋንዳ ካርታ

ዑጋንዳ፣ በአገሪቱ ታዋቂ ከኾኑ የሳፋሪ ብሔራዊ ፓርኮች በአንዱ፣ በጫጉላ ሽርሽር ላይ የነበሩ ጥንዶችንና አስጎብኚያቸውን የገደሉትን አጥቂዎች እያደነች እንደኾነ አስታወቀች፡፡

ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ፣ “የፈሪ ድርጊት” ሲሉ የገለጹትን የትላንት ማክሰኞ ጥቃት አውግዘው፣ አጥቂዎቹ በሕይወታቸው ዋጋ እንደሚከፍሉ ተናግረዋል።

በዚያ ጥቃት፣ አንድ እንግሊዛዊ እና ደቡብ አፍሪካዊ፣ ከዑጋንዳዊው አስጎብኚያቸው ጋራ እንደተገደሉ ፖሊስ ገልጿል፡፡

ፖሊስ፣ መሠረታቸውን በአጎራባቿ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ኮንጎ እንዳደረጉ የገለጻቸውን ታጣቂ ሚሊሻዎች፣ ለጥቃቱ ተጠያቂ አድርጓል።

ከአይኤስ ጋራ የተቆራኘውና ለጥቃቱ ፖሊስ ተጠያቂ ያደረገው የተባበሩት ዴሞክራቲክ ኃይሎች(ADF)፣ በሁከት እና ብጥብጥ በሚተራመሰው በምሥራቃዊ ኮንጎ፣ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ንጹሐን ዜጎችን እንደገደለ፣ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG