በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩጋንዳ ፖሊሶች በተጠርጣሪ ታሳሪዎች ላይ “ሰቆቃ ፈፅመዋል” በሚል ታሰሩ


በዩጋንዳ ውስጥ ፖሊሶች በተጠርጣሪዎች ላይ ሰቆቃ ፈፅመዋል በመባሉ ከፍተኛ ችግር ውስጥ መግባታቸው ተገለፀ።

በዩጋንዳ ውስጥ ፖሊሶች በተጠርጣሪዎች ላይ ሰቆቃ ፈፅመዋል በመባሉ ከፍተኛ ችግር ውስጥ መግባታቸው ተገለፀ።

ፕሬዚዳንቱና የአገር ውስጥ ሚኒስቴር ግን ጉዳዩ እልባት እንዲያገኝ በዚህ ሳምንት ውስጥ በይፋ መጠየቃቸው ታውቋል።

እአአ ባለፈው መጋቢት 17 ቀን የዩጋንዳ ፖሊስ ረዳት ተቆጣጣሪ ካማፓላ ውስጥ ይገደላሉ፣ ፖሊሶች ደግሞ ከአምስት ቀናት በኋላ 17 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር እንዳዋሉ አስታወቁ።

ሰዎቹ ከወር በኋላ ፍርድ ቤት ቢቀርቡም፣ ሂደቱ ለጋዜጠኞች ክፍት አልነበረም። ይሁንና ተጠርጣሪዎች ሰውነታቸው ላይ ሰቆቃና ወከባ እንደተፈፀመባቸው የሚያሳዩ ፎቶግራፎች ሾልከው ወጡ።

ባለፈው አስራ ቀን፣ እአአ ግንቦት 5 ቀን፣ ለ2ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ፣ “ተገርፈናል፣ ተደብድበናል” ብለው ያመለክታሉ።

“እጅና እግራችን ታስሮ እንዳለ ተደብድበናል” በማለት፣ የቆሰሉ የሰውነት ክፍሎቻቸውንም አሳይተዋል።

ሁኔታው በብሔራዊ ቴሌቪዥን ተላለፈና ከፍተኛ ሕዝባዊ ቁጣ ቀሰቀሰ።

የዩጋንዳ ፖሊስ ቃል አቀባይ አሳን ካሲንጌይ እንደተናገሩት፣ ሁለት ፖሊሶች ታስረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የዩጋንዳ ፖሊሶች በተጠርጣሪ ታሳሪዎች ላይ “ሰቆቃ ፈፅመዋል” በሚል ታሰሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:34 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG