በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለህክምና ወደውጭ ለመሄድ የሞከሩ የዩጋንዳ ምክር ቤት አባል ታሰሩ


ዩጋንዳ ዋና ከተማ ካምፕላ ውስጥ ለህክምና ወደውጭ ሀገር ለመሄድ የሞከሩ ታዋቂ ተቃዋሚን ፖሊሶች ማሰራቸውን ተከትሎ ተቃውሞ መቀስቀሱ ተዘግቧል።

ዩጋንዳ ዋና ከተማ ካምፕላ ውስጥ ለህክምና ወደውጭ ሀገር ለመሄድ የሞከሩ ታዋቂ ተቃዋሚን ፖሊሶች ማሰራቸውን ተከትሎ ተቃውሞ መቀስቀሱ ተዘግቧል።

በቅፅል ስማቸው ቦቢ ዋይን ተብለው የሚታወቁት የቀድሞ የሙዚቃ ኮከብ የአሁኑ የዩጋንዳ ምክር ቤት አባል ሮበርት ሮበርት ኪያጉላኒ ትናንት ማታ ካምፓላ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ታስረዋል።

ጠበቃቸው ለቪኦኤ እንደተናግሩት ከሆነ ቦቢ ዋይንን በርግጥ ታመው እንደሆነ ባለሥልጣናት እንዲያጣሩ ተብሎ ወደ መንግሥት ሆስፒታል ተወስደዋል።

ኪያጉላኒ በጥሩ ጤና ላይ ስላልሆኑ ለምርመራ ወደዩናይትድ ስቴትስ እንዲሄዱ በተሰጣቸው ምክር መሰረት ነው ሊጓዙ የነበረው።

ዛሬ ፖሊሶች ለህክምና ወደውጭ ሃገር ሊጓዙ የነበሩ ፍራንሲስ ዛአኪ የተባሉ ሌላ የምክር ቤት አባል አስረዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG