በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶማሊያ የገለልተኛ አገራት ንቅናቄ የግዛት አንድነቷን እንዲደግፍ ጠየቀች


ፎቶ ፋይል፦ ካምፓላ፣ ኡጋንዳ
ፎቶ ፋይል፦ ካምፓላ፣ ኡጋንዳ

የገለልተኛ አገራት ንቅናቄ ጉባኤ በኡጋንዳ መዲና ካምፓላ በመካሄድ ላይ ሲሆን፣ የሐማስ እና የእስራኤል ጉዳይ ዋና መነጋገሪያ ጉዳይ እንደሚሆን ይጠበቃል።

የሶማሊያ እና የፍልስጤማውያን ተወካዮች በበኩላቸው ለየራሳቸው ጉዳይ ድጋፍ ለማሰባሰብ እንደሚጥሩ አስታውቀዋል። ሶማሊያ የግዛት አንድነቷ እንዲጠበቅ ከንቅናቄው 120 ዓባል አገራት ድጋፍ እንደምትሻ ስትገልጽ፣ የፍልስጤም ተወካዮች ደግሞ አባል አገራት በጋዛ በመካሄድ ላይ ያለው ጦርነት የሚያበቃበትን መንገድ እንዲሹ ይጠይቃሉ ትብሏል።

ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ጋር ለወደብ እና ባሕር ኃይል አገልግሎት የሚውል ቦታ በቀይ ባሕር ላይ እንድታገኝ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት በቅርቡ መፈጸሟን አስመልክቶ ለቪኦኤ አስተያየት የሰጡትና በሶማሊያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቋሚ ፀሃፊ የሆኑት ሃምዛ አዳ ሃዶው፣

“ስምምነቱ የአገራችንን መብት፣ ሉአላዊነት እና አንድነት የሚጥስ በመሆኑ፣ የገለልተኛ አገራት ንቅናቄው ከጎናችን የሚቆም ከሆነ በአሁኑ ወቅት ያለንን ሰላም ጠብቀን ለመቆየት እንደምንችል እምነት አለን” ብለዋል።

ከንቅናቄው 120 ዓባላት መካከል ዘጠና ሶስቱ የተገኙበት ጉባኤ ዛሬ ሰኞ ሲከፈት፣ የዓረብ አገራት ተወካዮች የጋዛ ጉዳይ የጉባኤው ትኩረት እንዲሆን ጠይቀዋል። ተወካዮቹ “እስራኤል ጋዛ ውስጥ በመፈጸም ላይ ያለችው ጭካኔ የተሞላበት የዘር ማጥፋት” ብለው ለገለጹት ክስተት ጉባኤው ትክክለኛ ቋንቋ እንዲፈልግለትም ጠይቀዋል።

የዓባል አገራት መሪዎች በዚህ ሳምንት መጨረሻ ወደ ካምፓላ ከማቅናታቸው በፊት፣ ሶማሊያም ሆነች የፍልስጤም ወኪሎች ሌሎቹን የጉባኤው ተሳታፊዎች ለማሳመን እና አጀንዳቸው በውሳኔ ሃሳብ ውስጥ እንዲካተት ለማድረግ የአምስት ቀናት ግዜ አላቸው ተብሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG