በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኡጋንዳ በተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ላይ ጠንከር ያለ ሕግ አወጣች


ፎቶ ፋይል፦ የኡጋንዳ ፓርላማ
ፎቶ ፋይል፦ የኡጋንዳ ፓርላማ

የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በተመለከተ ዛሬ አንድ አዲስ ሕግ አጽድቋል። ሕጉ ከዚህ በፊት የነበሩትን እና በተመሳሳይ ጾታ ግኑኝነት ላይ ጠንከር ያለ ቅጣትን የያዙት አንቀጹችን መልሶ አካቷል።

በምዕራብ አገራት መንግሥታት ከፍተኛ ተቃውሞ በኡጋንዳ መንግሥት ላይ ከተደረገ በኋላ ፕሬዝደንቱ ዩዌሪ ሙሴቪኒ አዲሱ ረቂቅ እንደገና እንዲታይ ሃሳብ አቅርበው የነበረ ቢሆንም፣ ሸንጎው አዲሱን ሕግ በአንድ ተቃውሞ ብቻ አጽድቋል።

“ባህላችንን እንከላከላለን፤ ምዕራቡ ዓለም ኡጋንዳን አይገዛም ሲሉ” ተደምጠዋል የሸንጎው አፈ-ጉባኤ አኔት አኒታ አሞንግ።

አንድ ሰው የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ተከታይ በመሆኑ ብቻ እንደ ወንጀለኛ እንደማይቆጠር፣ ድርጊቱን በአደባባይ መፈጸም ግን እስከ ዕድሜ ልክ እስራት እንደሚያስቀጣ አዲሱ ሕግ ይደነግጋል። ሕጉን በተደጋጋሚ የሚጥስ ደግሞ በሞት እንደሚቀጣ ተደንግጓል።

XS
SM
MD
LG