በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኡጋንዳ የቆሻሻ ናዳ በርካቶች ሞቱ


በካምፓላ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ መደርመስ ተከትሎ የቀይ መስቀል መኮንን እርዳታ ለመስጠት እየተንቀሳቀሰ፤ ካምፓላ፣ ኡጋንዳ እአአ ነሃሴ 10/2024
በካምፓላ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ መደርመስ ተከትሎ የቀይ መስቀል መኮንን እርዳታ ለመስጠት እየተንቀሳቀሰ፤ ካምፓላ፣ ኡጋንዳ እአአ ነሃሴ 10/2024

በኡጋንዳ መዲና ካምፓላ በአንድ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ሥፍራ በተከሰተ ናዳ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 23 መድረሱን የከተማዋ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

ኪቲዚ በተሰኘ የሰሜን ካምፓላ ክፍል የሚገኘው ቆሻሻ ማጠራቀሚያ በሳምንቱ መጨረሻ የተናደው በአካባቢው የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ እንደሆነም ታውቋል።

አምስት ሕፃንናትን ጨምሮ 23 ሰዎች እንዲሁም እንስሳት በናዳው ሥር ተቀብረው ሕይወታቸው እንዳለፈ ተነግሯል።

የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በሕይወት የተረፉ ሰዎች ይገኙ እንደሁ ለማትረፍ የቆሻሻ ክምሩን ሲቆፍሩ፣ የሰለባዎቹ ቤተሰቦችም ተሰብስበው ሲያለቅሱ ተስተውሏል።

ክስተቱን “ብሔራዊ አደጋ” ብለው የገለጹት የከተማዋ ከንቲባ፣ በርካቶች አሁንም በቆሻሻው ክምር ውስጥ ተቀብረው ሊሆን እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል።

ከ28 ዓመታት በፊት የተመሠረተው የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ለመዲናዋ ካምፓላ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን፣ ከመጠን በላይ የታየው ክምችት ለአደጋ የሚያጋልጥ መሆኑን ከንቲባው ጨምረው አስታውቀዋል።

የሀገሪቱ ፕሬዝደንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ፣ የሠራዊቱ ልዩ ኃይሎች የነፍስ ማዳን ጥረቱን እንዲያግዙ አዘው፣ በአደገኛው ሥፍራው ሰዎች እንዲኖሩ ማን ፈቃድ እንደሰጠ ማወቅ እንደሚሹ ተናግረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG