በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩጋንዳ የሕገ መንግስታዊ ችሎት በተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ላይ የወጣውን ሕግ ደገፈ


በዩጋንዳ የሕገ መንግስታዊ ችሎት በተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ፈፃሚዎች ላይ እስከ ሞት የሚያደርስ ቅጣትን ያካተተ ሕግ ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኑን ተከትሎ፣ በሃገሪቱ የሚገኙ ዜጎች የተደበላለቀ አስተያየት በመስጠት ላይ ናቸው።

ከመብት ተሟጋች ቡድኖች እና ሌሎችም ዓለም አቀፍ አካላት ውግዘት የደረሰበት ሕግ እንዲሻር ዜጎች ጥያቄ አስገብተው የነበረ ሲሆን፣ በካምፓላ የሚገኘው ሕገ መንግስታዊ ችሎት ጥያቄያቸውን ውድቅ አድርጓል።

ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡ አንዳንድ ነዋሪዎች፣ ውሳኔው በተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ፈጻሚዎች ላይ ያለውን ችግር የሚያባብስ እንደሆነ ተናግረዋል። ሌሎች ደግሞ፣ ውሳኔው የአፍሪካ ነፃነት የታየበትና ሕዝቧ ማንነቱን ያስጠበቀበት ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ሕጉ በፓርላማው የፀደቀ መሆኑን እና ሕገ መንግስቱንም እንደማይቃረን የሕገ መንግስታዊ ችሎት ዳኞቹ አስታውቀዋል።

“ከተፈጠሮ ሥርዓት ጋራ የሚቃረን ነው” በሚል በዩጋንዳ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት በቅኝ ግዛት ወቅት በነበረው ሕግም የተከለከለ ነው።

የሃገሪቱ ፕሬዝደንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ አዲሱን ሕግ ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ በፊርማቸው አጽድቀውታል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG