በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ካምፓላ ከደረሱ ተከታታይ ፍንዳታዎች ጋር በተያያዘ ስድስት ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ


የዩጋንዳ ፖሊስ አገኘን ከሚሏቸው መረጃዎች ጋር
የዩጋንዳ ፖሊስ አገኘን ከሚሏቸው መረጃዎች ጋር

አራቱ ተጠርጣሪዎች ኢትዮጵያዊ መሆናቸው ተዘግቧል

እሁድለት በዩጋንዳ መዲና ካምፓላ ከደረሱ ተከታታይ ፍንዳታዎች ጋር በተያያዘ በትንሹ ስድስት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የዩጋንዳ ፖሊስ አረጋግጧል። አራተኛ ፍንዳታ ሊሆን ታስቦ ሳይፈነዳ የተያዘው በደረት የሚነገብ ፈንጂ መክሸፉን የገለጠው የፖሊስ መረጃ፤ ከታሳሪዎቹ የውጭ አገር ዜጎች መኖራቸውን ከመጠቆም ውጭ ስለማንነታቸው ያለው የለም።

የመንግስቱ ልሳን የሆነው የኒው ቪዥን ጋዜጣ ግን የደህንነት ምንጮችን ጠቅሶ አራቱ ታሳሪዎች ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን አስነብቧል።

በዩጋንዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ንጉሴ ባልቻ ለጊዜው በደንብ በዝርዝር የደረሰኝ ነገር የለም ቢሉም ታሰሩ ከተባሉት ሰዎች ጓደኞች አማካኝነት በደረሳቸው ዜና በመነሳት ተጠርጣሪዎቹ ኢትዮጵያዊ እንደሆኑ ሊያረጋግጡ ችለዋል።

XS
SM
MD
LG