በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኡጋንዳ ከሃያ አራት በላይ የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎችን አሰረች


የዩጋንዳ ፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቪኒ
የዩጋንዳ ፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቪኒ

በዚህ ሳምንት ውስጥ ከ24 በላይ ተቃዋሚ የፖለቲካ ደጋፊዎችን እንዳሰሩ የኡጋንዳ ፖሊሶች አስታወቁ።

በዚህ ሳምንት ውስጥ ከ24 በላይ ተቃዋሚ የፖለቲካ ደጋፊዎችን እንዳሰሩ የኡጋንዳ ፖሊሶች አስታወቁ።

የተቃዋሚ ደጋፊዎቹ መታሰር፣ ፕሬዚደንት ዮዌሪ ሙሴቪኒ እአአ በ2021 በሚካሄደው ምርጫ እንደገና ለመወዳደር ይችሉ ዘንድ ሕገ መንግሥቱን ይለውጣሉ ከሚለው ጥርጣሬ ጋር ሊገጣጠም ችሏል።

የኡጋንዳ ሕገ መንግሥት፣ አንድ የፕሬዚደንታዊ ምርጫ ተወዳዳሪ፣ ዕድሜው ከ75 ዓመት በታች መሆን እንዳለበት ይደነግጋል። ለ31 ዓመት ሥልጣን ላይ የቆዩት ሙሴቪኒ ግን በቀጣዩ ምርጫ 77 ዓመት ይሆናቸዋል።

ለማንኛውም ሙሴቪኒ፣ ለቀጣዩ ምርጫ እንደሚወዳደሩ በይፋ የተናገሩት ነገር የለም። እንዴውም ለተቃዋሚ ፓርቲዎቹ፣

“ሕገ መንግሥቱን ሊያሻሽል ነው” በሚለው ያልተረጋገጠ ወሬ ጊዜያችሁን አታጥፋ ማለታቸው ተሰምቷል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG