በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዮዌሪ ሙሴቬኒ የመሩት የጸረ ሙስና ሰልፍ


የዩጋንዳ ፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ በትናንትናው ዕለት በመሩት ጸረ ሙስና ሰልፍ ላይ ሙሰኞች የህዝብን ሃብት የሚመጠምጡቱ ተውሳኮች ናቸው ሲሉ ተናገሩ።

የዩጋንዳ ፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ነቃፊዎች ግን ፈጥነው ይሄ ለታይታ እንጂ ሌላ ትርጉም የለውም ብለዋል፡፡

ዩጋንዳ በዓለም ላይ በከፋ ደረጃ በሙስኛ ከዘቀጡ ሃገሮች መካከል የምትጠራ ስትሆን ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ላይ ጣታቸውን ይቀስራሉ፡፡

ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሺናል በአምና ሪፖርቱ ዩጋንዳን ሙስና በከፋ ሁኔታ ከተንሰራፋባቸው የአፍሪካ ሃገሮች አንዱዋ አድርጎ አስቀምጧታል።

አክሺን ኤይድ የተባለው ግብረ ሰናይ ድርጅትም በአብዛኛው ተጠያቂው መንግሥታቸው ሆኖ ሳለ የእርሳቸው ጸረ ሙስና ሰልፍ መምራት የሚገርም ነው ብሎታል፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG