በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጸረ ሙስና ሰልፍ በታቀደባት በካምፓላ ፖሊሶች ከፍተኛ ጥበቃ ሲያደርጉ ውለዋል


የዩጋንዳ ፖሊስ እና ወታደሮች በጥበቃ ላይ
የዩጋንዳ ፖሊስ እና ወታደሮች በጥበቃ ላይ

በዩጋንዳ መንግሥት የተከለከለው የዛሬው ጸረ ሙስና ሰልፍ በታቀደባት በመዲናዋ ካምፓላ ፖሊሶች በብዛት ወጥተው ጭር ያሉትን ጎዳናዎች ሲጠብቁ ታይተዋል።

ሀገሪቱን ለአርባ ዓመታት ገደማ በፈላጭ ቆራጭነት ሲመሩ የኖሩት ፕሬዚደንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ተቃዋሚ ሰልፈኞቹን "በእሳት አትጫወቱ" በማለት አስጠንቅቀዋል።

ተቃዋሚ መሪ ቦቢ ዋይን የብሄራዊ አንድነት መድረክ ፓርቲያቸው ጽሕፈት ቤት በፖሊስ እና በጦር ሠራዊት ወታደሮች ተከቧል ማለታቸውን ተከትሎ ትላንት ሰኞ ማታ ሦስት ተቃዋሚ የምክር ቤት አባላት ታስረዋል።

በአጎራባች ኬኒያ በአመዛኙ በወጣቶች በተመራው ጸረ መንግሥት ተቃውሞ የተነቃቃው እና ለዛሬ የታቀደው ጸረ ሙስና ተቃውሞ በኢንተርኔት አማካይነት የተደራጀ ሲሆን ሰልፈኛው ወደ ሀገሪቱ ምክር ቤት እንዲጓዝ አሳስቦ ነበር።

በከተማዋ ያሉ የፈረንሳይ ዜና ወኪል ዘጋቢዎች እንዳሉት ጭር ያሉት አብዛኞቹ ጎዳናዎች ታጥረዋል። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አድማ በታኝ ፖሊሶች ለጥበቃ ተሰማርተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG