አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በአሸባሪነት ተከሰው በእስር የሚገኙ ዜጎች ህገ-መንግስታዊ መብታቸው እንዲጠበቅ ጠየቀ። የጸረ ሽብርተኝነት አዋጁም ከአገሪቱ ህገ-መንግስት ጋር የሚጋጭ ነው አለ። አንድነት ይህን ያለው ዛሬ ባወጣው መግለጫ ነው።
እንድ የመንግስት ባለስልጣን በበኩላቸው ክሱ ትርጉም የለሽ ነው ብለዋል።
የአንድት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አንዱአለም አራጌ የጸረ ሽብሩ አዋጅ "ፖሊስ በበቂ ምክንያት ያመነ ከሆነ በድብቅ የሚደረግ የብርበራ ማዘዣ ከፍርድ ቤት እንዲሰጠው በጽሁፍ ወይም አስቸኳይ ሁኔታ ሲኖር በስልክ ፈቃድ ሊጠይቅ ይችላል" የሚል መሆኑን ገልጸው በጣም አሳዛኝ ነገር ነው ብለዋል።
አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈዱ ባለስጣን ግን "የጸረ ሽብር ህግ የህጉ ቀጥታ ንባባ ፍርድ ቤቶችን ጠይቆ ወይም አስፈቅዶ ማሰር ወይም መመርመር ይቻላል " ነው የሚለው ካሉ በኋላ ይህንን የውግዘት መግለጫ ያወጣው ተቃዋሚ ፓርቲ የህግ ምክር ቢጠይቅ የተሻለ ነው ሲሉ መክረዋል።