በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አንድነትና ሠላማዊ ትግል


አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ሰላማዊ ትግሉ የበለጠ ውጤታማ ሊሆን የሚችልባቸውን ሥልቶች የሚያጠና ኮሚቴ ማቋቋሙን አስታውቋል፡፡

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ሰላማዊ ትግሉ የበለጠ ውጤታማ ሊሆን የሚችልባቸውን ሥልቶች የሚያጠና ኮሚቴ ማቋቋሙን አስታውቋል፡፡

በእሥር ላይ እያሉ ድብደባ የተፈፀመባቸውን የአመራር አባሉን ጉዳይ በተመለከተም ከኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባለሥልጣናት ጋርም መወያየቱን ገልጿል፡፡

የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ዕሁድ የካቲት 18 ቀን ተሰብስቦ ያወጣው መግለጫ ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ ከጊዜ ወደ ጊዜ በአምባ ገነንነቱ እየገፋበት ነው ሲል ይከስሣል፡፡

የተለያዩ አሣሪና አስፈሪ አዋጆችን፣ መመሪያዎችን፣ ድንጋጌዎችን እያወጣና ለሕገመንግሥቱ እንኳ ሣይገዛ በተደጋጋሚ በአደባባይ በማንአለብኝነት ከሕግ በላይ እየሆነ ነው ሲልም መግለጫው ገዥውን ፓርቲ ይወነጅላል፡፡

በዚህም ምክንያት ነገሮች ከአቅም በላይ ሆነዋል የሚለው አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ግን በአዋጅ እስካልተከለከለ ድረስ በሰላማዊ ትግሉ እስከመጨረሻው እንደሚገፋበት በመግለጫው ያረጋግጣል፡፡

ብሔራዊ ምክር ቤቱ ባደረገው ስብሰባ ሁኔታውን ያገናዘበ ሠላማዊ ትግል እንዴት ባሉ ሥልቶች መካሄድ እንዳለበት የሚያጠና ኮሚቴ መሠየሙንም የፓርቲው አመራር አባል ዶ/ር ኃይሉ አርአያ ለቪኦኤ አስታውቀዋል፡፡

ዝርዝሩን ከመለስካቸው አምኃ ዘገባ ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG