በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አንዱዓለም በመንግሥት እጅ ሆነው ተደበደቡ


የአንድነቱ መሪ ከነፍሰገዳይ ጋር በአንድ ክፍል ታሠሩ፡፡

በእሥር ላይ የሚገኙት አቶ አንዱዓለም አራጌ ደኅንነታቸው አደጋ ላይ መሆኑን ፓርቲያቸው አንድነት ገልፆ ከዚህ ቀደም የተፈፀመባቸው በደል እንዲጣራና እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቋል፡፡

አንድነት በተጨማሪም መንግሥት ያወጣቸውን ሕጎችና ያፀደቃቸውን ዓለምአቀፍ ደንቦች እንዲያከብርም ጥሪ አቅርቧል፡፡

የተቃዋሚው አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ አባል አቶ አንዱዓለም አራጌ ተደብድበው ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ድርጅታቸው ማስታወቁ ይታወቃል፡፡

በእሥር ክፍላቸው ውስጥ ሣሉ በነፍስ ማጥፋት ወንጀል ፍርደኛ በሆነ ሰው ጥቃት ከደረሰባቸው በኋላ ለሕይወታቸው የሚሰጉ መሆናቸውም ተገልጿል፡፡

የዋናው ተቃዋሚ ፓርቲ የአንድነት መሪ የሃገሪቱ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በጉዳዩ ውስጥ ጣልቃ እንዲገባ ተማፅነዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዙት ዘገባዎች ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG