በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኡበር ለአውስትራሊያ ታክሲ አሽከርካሪዎች 178 ሚሊየን ዶላር ሊከፍል ነው


የኡበር አሽከርካሪ ለታክሲ በተመደበ ሥፍራ ቆሟል ሲድኒ፣ አውስትራሊያ እአአ መጋቢት 18/2024
የኡበር አሽከርካሪ ለታክሲ በተመደበ ሥፍራ ቆሟል ሲድኒ፣ አውስትራሊያ እአአ መጋቢት 18/2024

ኡበር የተሰኘው ግዙፉ ዓለም አቀፍ የታክሲ አገልግሎት ኩባንያ ወደ አውስትራሊያ ገበያ ሲገባ ገቢያቸውን ካጡ ታክሲ ነጂዎች ጋራ ለረጅም ጊዜ ያካሄደውን የሕግ ክርክር ለመቋጨት 178 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ሊከፍል ነው።

ኡበር ሰኞ ዕለት በጠቅላይ ፍርድቤት ይቀርባል ተብሎ ተጠብቆ የነበረ ቢሆንም፣ ከ8 ሺህ በላይ የታክሲ አሽከርካሪዎችን ወክለው የሚከራከሩት ጠበቃ ሞውሪስ ብላክበርን፣ ኡበር የገንዘብ ክፍያ ለማድረግ በመስማማቱ ክሱ እንደሚቋረጥ ተናግረዋል።

እ.አ.አ. በ2012 ኡበር ወደ አውስትራሊያ ገበያ ሲገባ የመኪና ባለቤቶች እና አሽከርካሪዎች ከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ እንደደረሰባቸው የገለፁት ጠበቃዋ "ለዓመታት፣ ድርጅቱ ጉዳት አድርሶባቸዋል ለምንላቸው ሰዎች ትክክለኛውን ነገር ለማድረግ ፈቃደኛ ሳይሆን ቆይቶ አሁን ኡበር አይኑን ገልጧል። በሺዎች የሚቆጠሩ አውስትራሊያውያን አንድ ላይ በመሆን ግዙፉ ዓለም አቀፍ ተቋም እጅ እንዲሰጥ አድርገዋል" ብለዋል።

ኡበር ባወጣው መግለጫ ጉዳዩ "ቀደም ብለው ከተደረጉ ውሳኔዎች የተነሳ ውስብስብ ችግር" መሆኑን እና ኩባንያው ከአስር ዓመት በፊት ኩባንያው ዓለም ላይ ሲስፋፋ የመጓጓዣ አገልግሎትን በጋራ የመጠቀም ህግ አለመኖሩን አብራርቷል።

ይህ አይነቱ የትራንስፖርት አገልግሎት አውስትራሊያ ውስጥ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ የመጓጓዝን ኢንዱስትሪ እንዳሻሻለው በማመልከትም፣ ለተጠቃሚዎች የበለጠ ምርጫ እና የተሻሻለ ተሞክሮ ማምጣቱን፣ እንዲሁም በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ አውስትራሊያውያን አዲስ የገቢ ምንጭ መፍጠሩን ገልጿል።

በዚህ የገንዘብ ክፍያ ስምምነትም ለረጅም ጊዜ የኖሩ እና ውስብስብ ያላቸውን ችግሮች ወደ ኋላ በመተው አሁን ላይ ለማተኮር እንደሚያስችል፣ ኡበር ጨምሮ አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG