ዋሽንግተን ዲሲ —
የዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ባለሥልጣናት የደሃቢ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አካል በሆነው ስፍራ የሚገኙ ሦስት የነዳጅ ማጠራቀሚያ ታንከሮች በድሮን መሆኑ የተገመተ ጥቃት የደረሰባቸው መሆኑን ተናገሩ፡፡
የአገሪቱ መንግሥት ዜና አገልግሎት ባለሥልጣናቱን ጠቅሶ እንዳስታወቀው በደረሰው ጥቃት ቢያንስ ሶስት ሰዎች የሞቱ ሲሆን ሌሎች ስድስት ደግሞ መቁሰላቸው ተመልክቷል፡፡
ከሟቾቹ ሁለት ህንድና አንድ የፓኪስታን ዜጎች እንደሚገኙበትም ተነገሯል፡፡
ፖሊሲ ሁኔታው እየተጣራ መሆኑን ቢገልጽም የየመን ሁቲዎች ዛሬ ሰኞ በሰጡት መግለጫ ወደ ዩናይትድ አረብ ኤምሬት ጠልቆ የሚገባ ጥቃት የሰነዘሩ መሆናቸውን ቢያስታውቁም ስለ ሁኔታው ግን ዝርዝር መግለጫ አልሰጡም፡፡
የዩናይትድ አረብ ኤምሬት እኤአ ከ2015 ጀምሮ የየመን ሁቲዎችን የሚወጋውና በሳኡዲ አረብያ የሚመራው የጦር ህብረት አባል መሆንዋ ይታወቃል፡፡
ዘገባዎቹ የተገኙት ከአሶሼይትድ ፕሬስና አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ነው፡፡