በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኳድ ግሩፕ በቻይና ባህር የሚታየው ወታደራዊ እንቅስቃሴ አሳስቦኛል አለ

ኳድ ግሩፕ በመባል የሚታወቁት አገራት የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች አጨቃጫቂ በሆኑት በደቡብ እና ምሥራቅ የቻይና ባህር ግዛቶች ላይ የሚታየው ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንዳሳሰባቸው ዛሬ አስታውቀዋል።

ቻይና ላይ ባነጣጠረው በዚሁ መልዕክታቸው የአሜሪካ፣ አውስትራሊያ፣ ሕንድና ጃፓን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኒው ደልሂ ተሰብስበው ቻይናን በስም ሳይጠቅሱ በኢንዶ ፓሲፊክ ባህር ላይ የሚታየው ወታደራዊ እንቅስቃሴ እና የሌሎች አገራት በባህር ዳርቻቸው የሚያደርጉትን የተፈጥሮ ሃብት ልማት እንቅስቃሴ ለማስተጓጎል የሚደረግ ሙከራ እጅግ አሳስቦናል ብለዋል።

ዓለም አቀፍ የባህር ላይ ሕግጋት እንዲከበሩ የጠየቁት የአገራቱ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ በተናጥል የሚደረግንና ቀድሞ የነበረውን የባህር ላይ ይዞታን ለመለወጥ እንዲሁም ውጥረትን ለመጨመር የሚደረግን እንቅስቃሴ እንደሚቃወሙ አስታውቀዋል።

ቻይና ‘የደቡብ ቻይና ባህር’ ተብሎ የሚጠራው የውሃ አካል ሉአላዊ ግዛቷ እንደሆነ ታስታውቃለች። በአካባቢው ከሚገኙ አገራትም በዚህ ባህር ይገባኛል ጉዳይ ውዝግብ ውስጥ ገብታለች። ወታደራዊ ጣቢያም በሠራችው ደሴት ላይ አቋቁማለች።

ኳድ የተሰኘው ቡድን ራሱን ስልታዊ መድረክ ብሉ ሲጠራ ቤጂንግ ግን ዋሽንግተን አጋሮቿን አስተባብራ ልትከባት የፈጠረችው ቡድን ነው ስትል ትከሳለች።

XS
SM
MD
LG