በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዚምባቡዌ የዩናይትድ ስቴትስ የቪዛ ገደብ ላይ እንዳስቆጣት ገለጸች


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን

የዚምባብዌ ገዥው ዛኑ ፒ ኤፍ ፓርቲ በደቡባዊ አፍሪካዊቷ ሀገር ዴሞክራሲን በማናጋት በተወነጀሉ ሰዎች ላይ ያነጣጠረው አዲሱ የዩናይትድ ስቴትስ የቪዛ ገደብ ፖሊሲ ያስቆጣው መሆኑን አስታውቋል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን የቪዛ ገደቡን በዚህ ሳምንት ይፋ አድርገዋል፡፡

ሐራሬ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ቃል አቀባይ ሎረንስ ሶቻ ለቪኦኤ እንደተናገሩት አዲሱ የቪዛ ገደብ ፖሊሲ ዲሞክራሲን ለመናድ ተጠያቂ ወይም ተባባሪ ናቸው ተብለው በሚታመኑ ግለሰቦች ላይ ተፅዕኖ ይኖረዋል።

እንዲህ ያሉ እርምጃዎች “በሙስና መሳተፍን፣ የምርጫውን ሂደት የሚያበላሽ ጉቦን ጨምሮ፣ በፍትህ አካላት ገለልተኛ አሰራር ውስጥ ጣልቃ መግባት፣ በሀገሪቱ ሰብዐዊ መብቶች ካለአግባብ መጠቀምን ወይም መጣስን ሊያካትቱ ይችላሉ” ብለዋል፡፡

የቪዛ ክልከላው ያተኮረው በተወሰኑ ግለሰቦች እንጂ በዚምባቡዌ ዜጎች ላይ አለመሆኑን ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡

የገዢው ፓርቲ ቃል አቀባይ ፋራይ ሙሮይዋ ማራፒራ “እንደ ዛኑ ፒ ኤፍ ፓርቲ በዚህ የአሜሪካ መንግስት አዲስ እንቅስቃሴ አልተገረምንም። መንግሥት የመቀየር ዓላማ እንዳላቸው ሁላችንም እናውቃለን” ብለዋል፡፡

“ተንኮላቸው በሙሉ በነሀሴ ወሩ ምርጫ ከሽፎባቸዋል” ሲሉ ያከሉት ቃል አቀባዩ “ የቪዛ እቀባው ብዙ ተጽዕኖ ይኖረዋል ብለው እንደማይገምቱም ገልጸዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG