በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ በአንዳንድ የሶማሊያ ባለስልጣናት ላይ የቪዛ ገደብ ጣለች።


ዩናይትድ ስቴትስ “በሶማሊያ ዲሞክራሲያዊ ሂደቶችን አደናቅፈዋል” በሚል በወነጀለቻቸው የዚያች አገር ባለስልጣናት እና አንዳንድ ግለሰቦች ላይ ወደ ዋሽንግተን የሚያደረጉ ጉዞዎችን የሚከለክል የቪዛ ገደብ ጣለች።

ትላንት ሊጠናቀቅ ታቅዶ የነበረውን የፓርላማ አባላት ምርጫ ወደ መጭው መጋቢት 6, 2014 ዓም መግፋታቸውን ተከትሎ አገራቸው የቪዛ እገዳ ውሳኔ ማሳለፏን የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንተኒ ብሊንከን አስታውቀዋል።

"አሁን በዚህ ፖሊሲ መሰረት፣ በፈጸሙት አደናቃፊ የሆነ ምግባር ተጠያቂ ለማድረግ በበርካታ የሶማሊያ ባለስልጣናት እና ግለሰቦች ላይ የቪዛ እገዳ ጥለናል" ነው ያሉት።

ብሊንከን ይህን ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚንስትር በትላንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ ነው።

XS
SM
MD
LG