በአሜሪካ ም/ቤት የሪፐብሊካን ፓርቲው የኒው ዮርክ ተወካይ የሆኑት ጆርጅ ሳንቶስድ ከደጋፊዎቻቸው ክሬዲት ካርድ ሰርቀዋል የሚል ክስ ተመሥርቶባቸዋል።
ሳንቶስ በምርጫ ዘመቻቸው ወቅት የገንዘብ ድጋፍ ያደረጉላቸውን ሰዎችን የግል መረጃ በመሰብሰብ፣ ደጋፊዎቹ ፈቃድ ያልሰጡት በአሥር ሺሕዎች የሚቆጠር ዶላር ከክሬዲት ካርዳቸው ላይ ክፍያ እንዲፈጸም አድርገዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል። ከተሠረቀው ገንዘብ ውስጥ ከፊሉ በግል ባንካቸው ገቢ ሆኗልም ብለዋል አቃቢያነ ሕጎች፡፡
ሳንቶስ ከ 44ሺሕ ዶላር በላይ ግለሰቦቹ ሳይፈቅዱ ከክሬዲት ካርዳቸው ላይ ክፍያ እንዲፈጸም አድርገዋል፤ በተጨማሪም ከአንድ ደጋፊ ላይ 12ሺሕ ዶላር ወጪ እንዲሆን ካደረጉ በኋላ አብዛኛውን ገንዘብ ወደ ግል ባንካቸው አዙረዋል ሲል ክሱ አመልክቷል።
የኒው ዮርኩ ሪፐብሊካን በተጨማሪም፣ ለኮንግረስ ሃብታቸውን በሚያስመዘግቡበት ግዜ ዋሽተዋል ተብሏል።
ትናንት አዲስ የቀረበው ክስ፣ ባለፈው ግንቦት የቀረብዉን ክስ ይተካል ተብሏል። በምርጫ ዘመቻ ወቅት ከተሰበሰብው ገንዘብ ላይ ለግል ጥቅም አውለዋል የሚል ክስ ባለፈው ግንቦት ቀርቦባቸው ነበር።
በባንክ አካውንታቸው ውስጥ 8 ሺሕ ብር ብቻ እያለ፣ ለምርጫ ዘመቻቸው 44 ሺሕ ዶላር አበድሬያለሁ ብለው ለፌዴራሉ የምርጫ ኮሚሽን ዋሽተዋል ሲል ክሱ በተጨማሪ አመልክቷል።
መድረክ / ፎረም