በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ በዘንድሮ የኣትላንታ የስፖርት በዓል የክብር እንግዳ ሆነው ይገኛሉ


በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን ስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን ለዘንድሮው 28ኛ ዓመታዊ በዐሉ ዳኛ ብርቱካንን በክብር እንግድነት መምረጡ ጥቂት ያነጋግር ቢሆንም፣ ባለፈው ሰሞን መፍትሔ ማግኘቱን ፌዴሬሽኑ አመልክቷል

ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ፣ ፌዴሬሽኑ እአአ ከመጪው ሐምሌ 3-9-2011 ዓም አትላንታ ከተማ ውስጥ ለሚያካሂደው ዓመታዊ በዐል፣ በክብር እንግድነት እንደተጠቆሙና በአብላጫ የቦርዱ አባላት ድምፅም እንደተመረጡ ይታወቃል።

የእርሳቸው መመረጥ ግን ለጥቂት ጊዜ ሲያወያይ መሰንበቱ፣ እንዲያውም ፌዴሬሽኑ በድምፅ ብልጫ ያሳለፈውን ውሳኔ መሳቡና ያም ውዝግብ መቀስቀሱ አይዘነጋም።

ባለፈው ሰሞን ግን የፌዴሬሽኑ ብዙኃን የቦርድና የሥራ አስፈጻሚ ኰሚቴ አባላት አትላንታ ከተማ ተገናኝተው፣ የወይዘሪት ብርቱካንን ምርጫ ደግፈው፣ ቀደም ሲል ውሳኔው መሻሩም አግባብ እንዳልሆነ አምነው፣ ወይዘሪት ብሩካን ሚደቅሳ ዘንድሮ አትላንታ ከተማ የሚደረገው የ28ኛ ዓመት የሰሜን አሜሪካ የስፖርትና የባሕል ፌዴሬሽን የክብር እንግዳ መሆናቸውን የሚያወሳ መግለጫም አውጥተዋል።

ከኣዲሱ ኣበበ ጋር ያደረጉትን ሙሉ ውይይት ያድምጡ

XS
SM
MD
LG