በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመከላከያ ሚኒስትሩ ኦስቲን ከምክር ቤቱ ፊት ይቀርባሉ


የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን
የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን

የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን ስለካንሰር ምርመራቸውና እሱንም ተከትሎ ሆስፒታል ስለመግባታቸው ለፕሬዚዳንት ባይደን ማሳወቅን ጨምሮ ለሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት ለምን ይፋ እንዳላደረጉ ለተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ቃላቸውን እንደሚሰጡ የምክር ቤቱ ቃል አቀባይ ትናንት ማስከኞ አስታውቀዋል፡፡

የመከላከያ ሚኒስትሩ ሎይድ ኦስቲን፣ እኤአ የካቲት 29 ከምክር ቤቱ የወታደራዊ አገልግሎት ኮሚቴ ፊት ቀርበው ሆስፒታል መግባታቸውን ለምን እንዳላሳወቁ ያስረዳሉ ሲል የመከላከያ ሚኒስቴር አረጋግጧል፡፡

ኦስቲን ባላፈው ሳምንት በቴሌቭዥን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ለባይደን እና ለከፍተኛ ባለሥልጣናት በቅርቡ ስለነበራቸው የፕሮስቴት እጢ ካንሰር ህክምናቸው በወቅቱ አስቀድመው ባለመናገራቸው ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡

የጤናቸው መታወክ በጣም ያስደነገጣቸው መሆኑንም ሚኒስትሩ አከለው ገልጸዋል፡፡

የቀደሞውን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕን ጨምሮ አንዳንድ እውቅ የሪፐብሊካን አባላት ኦስቲን ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ጠይቀዋል፡፡

አንድ ባለሥልጣን እንደተናገሩት ፕሬዚዳንት ባይደን ለኦስቲን የሚሰጡትን ድጋፍ ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG