በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ እያሽቆለቆለ ያለው የደቡብ ሱዳን ሁኔታ እንዳሳሰባት ገለጸች


ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ
ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ

ትናንት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ባወጡት መግለጫ በቅርቡ በደቡብ ሱዳን ህዝባዊ መከላከያ ኃይሎች እና በሱዳን ህዝብ ነጻ አውጭ ጦር ተቃዋሚ አንጃ ኃይሎች መካከል አፐር ናይል ክፍለ ግዛት ውስጥ የተከሰቱትን ግጭቶች ጨመሮ በሀገሪቱ ውጥረቱ እየተባባሰ መምጣቱ ዩናይትድ ስቴትስን አሳስቧታል ብለዋል።

ሁለቱም ወገኖች በሰላም ሥምምነቱ ያለባቸውን ግዴታ ሙሉ በሙሉ እንዲያከብሩ እና ጠብ አጫሪ የሆኑ ንግግሮች በአስቸኳይ ማቆም ይኖርባቸዋል ሲሉ አሳስበዋል።

የሱዳን ህዝብ ነጻ አውጭ ጦር ተቃዋሚ አንጃ በሰላም ሥምምነቱ ውስጥ ከተካተቱት የተኩስ አቁም መቆጣጠሪያ እና ማረጋገጫ ሥርዓቶች በሙሉ አልቀበልም ማለቱ የሰላም ውሉን የሚጎዳ እድራጎት እንደሁነ ገልጸው ተቆጣጣሪዎቹ አካላት በቅርብ ጊዜ የደረሱትን ግጭቶች መርምረው የድርጊቱን ሃላፊዎች በተተያቂነት ለመያዝ ጥረት እያደረጉ በመሆኑ በአስቸኳይ አቋሙን እንዲቀለብስ አሳስበዋል።

የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር እና ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ሪያክ ማቻር ውጥረቱን ለማብረድ እና በሰላም ውሉ ያለባቸውን ግዴታ ለማክበር የተቻላቸውን ሁሉ እንዲያደርጉ ዩናይትድ ስቴትስ ጥሪ ታደርጋለች ብለዋል።

XS
SM
MD
LG